Saturday, 17 July 2021 14:38

አንድ ወጣት ማዕከል በአበበ ቢቂላ ስም ተሰየመ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 “ታለንት የወጣቶች ማህበር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች ማህበር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና የበጎ ፍቃድ ማስተባበር ቢሮና ከኢፌድሪ የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከሚገኙት 113 የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት መካከል በአራት ኪሎ የሚገኘውን ወረዳ ዘጠኝ ማዕከልን በእውቁና የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ የዓለም ኦምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ በሆነው ሻምበል አበበ ቢቂላ ስም ሰየመ፡፡
“Abebe Bikela Youth Centere” የተሰኘውን ይህን ማዕከል ሞዴል ሰርቶ ማሳያ ለማድረግና ወደ ሌሎችም ወጣት ማዕከላት  ለማስፋፋት እንዲቻል የተለያየ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ትላንት ከቀኑ 8፡00  ጀምሮ ሀላፊዎቹ በማዕከሉ በሰጡት መግለጫና ማዕከሉን ይፋ የማድረግ ሥነ- ሥርዓት ላይ  አስተዋውቀዋል፡፡
ማዕከሉ በጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ መሰየሙ ለወጣቶች የጥረት፣የቆራጥነትና የአሸናፊነት ተምሳሌት እንዲሆን በማሰብ ነውም ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ለአበበ ቢቂላ ስኬት ወሳኝ ሚና የነበረውን ስዊዲናዊ አሰልጣኝ ኦኒ ኒስካኔንን ለመዘከር ከማዕከሉ 3ኛው ፎቅ በዚሁ ስዊዲናዊ ሥም እንዲሰየም መወሰኑም ታውቋል፡፡
ማዕከሉ በዋናነት የወጣቶች የስራ ፈጠራ ማዕከል እንዲሆን የሚያስችሉ የተለያዩ ዕቅዶች ተዘጋጅተውለትና ህንፃውም ሳቢና ማራኪ እንዲሆን ታስቦ ከወጣቶች የተውጣጡ ባለሙያዎች ተመካክረው ዲዛይን ተሰርቶለታል፡፡ በዕለቱም በርካታ ወጣቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ማዕከሉን ጎብኝተዋል፡፡

Read 587 times