Monday, 26 July 2021 19:29

“በስቅለቱ ቀን እና ሌሎች ተረኮች” ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ደራሲና ተርጓሚ አብይ ጣሰው ወደ አማርኛ የእውቅ ዓለም አቀፍ ደራሲያን አጫጭር ታሪኮች መድበል “በስቅለቱ ቀን እና ሌሎች ታሪኮች” የተሰኘ መፅሀፍ ከሰሞኑ ገበያ ላይ ውሏል።
በዚህ  መፅሐፍ ከ15 በላይ የእውቅ ደራሲያን አጫጭር ታሪኮች የተካተቱ ሲሆን የአንገቷን ቸኮቭ፣ የሊዮ ቶልስቶዮን፣ የአብደላህ  ካሃር፣ የኦስታ ፕቪንሲያ እና የሌሎችም እውቅ ድርሰቶች ይገኙበታል። በ130 ገጾች የተቀነበበውና ከኤዞፕ ክላሲክ ከሚታተሙ የእውቅ ደራሲያን ስራዎች የተመረጡትን የያዘው ይህ ቅፅ 1 መፅሐፍ፤ በ150 ብር ገበያ ቀርቧል፡፡ ቅፅ 2 በቅርቡ ለንባብ እንደሚበቃም ተጠቁሟል፡፡

Read 12576 times