Print this page
Wednesday, 28 July 2021 00:00

በሩስያ በወርቅ የተለበጠ የሙሰኛ ፖሊሶች መጸዳጃ ቤት ተገኘ

Written by 
Rate this item
(0 votes)


              አንድ የወንጀል ድርጊትን ለመመርመር በሩስያ ገጠራማ አካባቢ ወደሚገኝ ቅንጡ መኖሪያ ቤት ያመሩ የአገሪቱ ፖሊሶች፣ እጅግ ውድ በሆነ ወርቅ የተለበጠ የሙሰኛ ፖሊሶች መጸዳጃ ቤት ማግኘታቸው ተነግሯል፡፡
ስታቭሮፑል በተባለው የአገሪቱ አካባቢ የትራፊክ ፖሊስ ሃላፊ የሆኑ አንድ ኮሎኔል ሙስና በመቀበል ሃሰተኛ የይለፍ ፈቃድ በመስጠት የፈጸሙትን ወንጀል ለማጣራት ወደ ስፍራው ያመሩ ፖሊሶች፣ በቅንጡው ቤት ውስጥ በወርቅ የተለበጠውን መጸዳጃ ቤት ማግኘታቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡
መርማሪዎቹ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብና እጅግ ውድ የቅንጦት መኪኖችን ጭምር ማግኘታቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ ኮሎኔሉና አምስት ግብረ አበሮቻቸው ለአመታት በሙስና ከ225 ሺህ ዶላር በላይ ማካበታቸውን ለማረጋገጥ መቻላቸውን እንዳስታወቁም ገልጧል፡፡

Read 2595 times
Administrator

Latest from Administrator