Print this page
Saturday, 31 July 2021 00:00

አትሌት ሰለሞን ባረጋ በቶክዮ በ10 ሺ ሜትር የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸነፈ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ትላንት በጃፓን ቶክዮ ኦሎምፒክ በተደረገው የ10ሺ ሜትር የሩጫ ውድድር  አትሌት ሰለሞን ባረጋ ርቀቱን በ27፡43.22 በማጠናቀቅ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኗል። በ10ሺና በ5ሺ ሜትር የዓለም ሪከርዶችን የያዙት ኡጋንዳዊ  አትሌት ቼፕቴጊ እንዲሁም ሌላ ኡጋንዳዊ አትሌት ጄፕቴጊ ቼፕሊሞ ውድድሩን የ2ኛና 3ኛ ደረጃን አግኝተዋል። ሌሎቹ የኢትዮጵያ አትሌቶች አትሌት በሪሁ አረጋዊ በ4ኛ ደረጃ  እንዲሁም አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በ8ኛ ደረጃ ውድድሩን አጠናቅቋል።
ከ32ኛ ኦሎምፒክ በፊት ኢትዮጵያ በተሳተፈችባቸው ባለፉት 13 ኦሎምፒኮች  በ10ሺ ሜትር ወንዶች 5 የወርቅ፤ 2 የብርና 5 የነሀስ ሜዲሊያዎችን የሰበሰበች ሲሆን የሰለሞን ባረጋ ድል  በ10ሺ ሜትር 6ኛ የኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ሆኖ ተመዝግቧል።
በ2012 እ.ኤ.አ በለንደን ኦሎምፒክና በ2016 በሪዮ ዲጀነሪዮ ኦሎምፒክ፣ የወርቅ ሜዳሊያዎችን አከታትሎ ማሸነፍ የቻለው እንግሊዛዊ አትሌት ሙፋራህ ሲሆን ሰለሞን ባረጋ የኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ክብርን ያስመለሰው ከሁለት ኦሎምፒኮች በኋላ ነው።
በ10ሺ ሜትር ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ውጤት በብር ሜዳሊያ ያስመዘገበው አትሌት ማሞ ወልዴ በ1968 እ.ኤአ በሜክሲኮ ኦሎምፒክ ነበር። ከዚም በ1972 እ.ኤአ በሙኒክ ኦሎምፒክ ምሩጽ ይፍጠር የነሃስ፤ በ1992 እ.ኤ.አ በርሴሎና ኦሎምፒክ አዲስ አበባ የነሀስ፤ በ1996 እ.ኤ.አ በአትላንታ ኦሎምፒክ ኃይሌ ገ/ስላሴ የወርቅና በ2000 እ.ኤ.አ በሲድኒ ኦሎምፒክ ኃይሌ ገ/ስላሴ የወርቅ እንዲሁም አትሌት  አሰፋ መዝገቡ የነሀስ፤ በ2004 እ.ኤ.አ በአቴንስ ኦሎምፒክ ቀነኒሳ በቀለ የወርቅና አትሌት ስለሺ ስህን የብር፤ በ2008 እ.ኤ.አ በቤጂንግ ኦሎምፒክ ቀነኒሳ በቀለ የወርቅና  ስለሺ ስህን ብር እንዲሁም በ2012 እ.ኤአ በለንደን ኦሎምፒክ ታሪኩ በቀለ የነሀስ ሜዳሊያን አግኝተዋል።



Read 8253 times
Administrator

Latest from Administrator