Tuesday, 03 August 2021 18:24

“ከማዕዘኑ ወዲህ” መፅሐፍ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  የህግ ባለሙያው ወጣት ዳግማዊ አሰፋ ሁለተኛ ሥራ የሆነውና በራሱ የእውነተኛ አሳዛኝ የህይወት ገጠመኝ ላይ የሚያጠነጥነው “ከማዕዘኑ ወዲህ” መፅሐፍ በቅርቡ ለንባብ የበቃ ሲሆን ነሀሴ 2013 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ እንደሚመረቅ ታውቋል።
ወጣቱ የህግ ባለሙያ ገና በአፍላ እድሜው በጥብቅና ሙያ ላይ እያለ ከባለጉዳይ በተተኮሰበት ጥይት ጉሮሮው ተበስቶ በህክምና ላይ እያለ ከአምስት ጊዜ በላይ ከሞት አፋፍ ተመልሶና ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶበት ከአንገቱ በታች ያለው ሰውነቱ በሙሉ ባይንቀሳቀስም የደረሰበትን አደጋ፣ ከሞት ያመለጠበትን አሁን ያለውን እሱነቱን ለመቀበል የተቸገርንበትን ሁኔታ “አዲስ ህይወት” የተሰኘ የመጀመሪያ መፅሀፍ ለአንባቢ አድርሷል።
በሁለተኛው መፅሀፉ ደግሞ ከራሱ ጋር ሙግት ገጥሞ አሁን ያለውን  ማንነቱን ለመቀበል የሄደበትን እርቀት፣ አሁን የተጎናጸፈውን የመንፈስ ጥንካሬ፣ ይህን ሁሉ አደጋ ያደረሰበትን ሰው ይቅር ያለበት ከፈጣሪው ጋር ሙግት አቁሞ ያመሰገነበትን አጠቃላይ ሂደት ያሰፈረበት ነው። “ከማዕዘን ወዲህ” መፅሐፍ በነሀሴ ወር መጀመሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የሚመረቅ ሲሆን በ206 ገጽ ተቀንብቦ በ150 ብር እና በ10 ዶላር ለገበያ ቀርቧል።

Read 6551 times