Saturday, 07 August 2021 14:17

“እኔስ ለሀገሬ 2” የኪነ-ጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  በሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት በየወሩ የሚካሄደው የኪነ-ጥበብ ምሽት የዚህ ወር መሰናዶ “እኔስ ለሀገሬ 2” በሚል መሪ ቃል የፊታችን ሰኞ ነሀሴ 3 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል። በዕለቱ ወግ፣ ዲስኩር ግጥምና ሙዚቃ ለታዳሚ የሚቀርብ ሲሆን፣ ፍሰሃ እሸቱ (ዶ/ር)፣ አበባው አያሌው (ረ/ፕ)፣ ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣ እውቁ ፖለቲከኛና ደራሲ አንዱአለም አራጌ፣ ዶ/ር ሙሉአለም ተገኝወርቅ፣ ገጣሚ አደም ሁሴን (የአዳማው)፣ ገጣሚያኑ ባንቻየሁ አሰፋ፣ መቅደስ ሞገስና ነብያት ሙላት ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
ድምፃዊ ታሪኩ ካንጊሲ (ዲሽታ ጊና) ከአድዋ ባንድ ጋር ሙዚቃ የሚያቀርብ ሲሆን የመግቢያ ዋጋው 100 ብር እንደሆነና ትኬቶቹን በጃዕፈር፣ ዮናስ፣ ዘውዱ፣ እውቀት በርና ጦቢያ መፅሐፍት መደብሮች ማግኘት እንደሚቻል አዘጋጁ ሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት ገልጿል።

Read 11153 times