Saturday, 14 August 2021 11:52

“እጅ የበዛበት የኦሮሞ ፖለቲካና ኢትዮጵያዊነት” መፅሐፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

      በጋዜጠኛና ደራሲ ዮሴፍ ከተማ ተዘጋጀው “እጅ የበዛበት የኦሮሞ ፖለቲካና ኢትዮጵያዊነት” መፅሐፍ ዛሬ ነሐሴ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል። መፅሐፉ በዋናነት በብሔር ፖለቲካ፣ በኦሮሞ ፖለቲካ ውስጥ ባለፉት ዓመታት ሲቀነቀኑ የነበሩትን ትርክቶችና ውጤታቸውን በስፋት የሚቃኝ ሲሆን፣ የተለያዩ ፍላጎቶችንና አስተሳሰቦችንም ደራሲው ከተገኘበት የኦሮሞ ህዝብ ጥቅም አንጻር እውነቱና የሚጠቅመው የቱ ነው ሲል ይጠይቃል።
በምረቃ ስነ-ስርቱ ላይ አንጋፋ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች ደራሲያንና ጋዜጠኞች የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም መካከል አንጋፋው ፖለከኛና ደራሲ አበበ አካሉ፣ ደራሲና ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ፣ የሕግና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ቴዎድሮስ መብራቱ፣ ሲሳይ መንግስቴ (ዶ/ር)፣ ደራሲና ተርጓሚ ውብሸት ስጦታውና ሌሎችም ታድመው በመጽሐፉ ዙሪያ ፣በወቅቱ የሀገራችን ሁኔታና በመፍትሄ ሃሳቦች ዙሪያ ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል።
መፅሐፉ በ293 ገጽ ተቀንብቦ በ135 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ደራሲና ጋዜጠኛ ዮሴፍ ከተማ ከዚህ ቀደም “እሬቶ” የተሰኘ ልብወለድ መፅሐፍ የበገና ታሪክና ማስተማሪያ መፅሐፍና ሌሎችንም በብዕር ስም ያሳተማቸውን መፅሐፍት ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም።

Read 12858 times