Saturday, 14 August 2021 11:58

የጨለማው ፍኖት” መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በደራሲ ቶማስ ሳህሌ የተዘጋጀው “የጨለማው ፍኖት” መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ። በአዕምሮ ህመም፣ በፍቅር፣ በጥላቻና አሳዛኝ በሆኑ ታሪኮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ይህ መጽሐፍ ለደራሲው የመጀመሪያ ሥራው ሲሆን ሰሞኑን አራት ኪሎ ኢክላስ ህንፃ ስር በተከፈተው በዋሊያ መፅሐፍት “ክረምትና ንባብ” በተሰኘው የመፅሐፍት አውደ ርዕይና ኪነ-ጥበባዊ ሁነቶች ላይ ከተመረቁት መፅሐፍት አንዱ ሆኗል። በ140 ገፅ የተቀነበበው መፅሐፉ በ140 ብር ለገበያ ቀርቧል።
ደራሲው ቶማስ ሳህሌ ከዚህ ቀደም “አቦል” በተሰኘውና የበርካታ ደራሲያንን ስራ ባካተተው መፅሐፍ ውስጥ ሁለት ታሪኮችን በማበርከት ተሳትፎ ያደረገ ሲሆን “የጨለማው ፍኖት” የመጀመሪያ ስራው እንደሆነ ታውቋል።


Read 12835 times