Saturday, 21 August 2021 00:00

አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ብድር ለመልቀቅ ፈቃደኛ አይደሉም ተባለ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

ዓለማቀፍ የገንዘብ ተቋምና የቻይናው ኤግዚም ባንክን ጨምሮ በዓመቱ ለኢትዮጵያ ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለማበደር ተስማምተው የነበሩ አለማቀፍ የገንዘብ ተቋማት ብድሩን ለመልቀቅ ፍቃደኛ አልሆኑም ተባለ።
አለማቀፉ የልማት ትብብር ማህበር 3.3 ቢሊዮን ዶላር፣ የቻይናው ኤግዚሞ ባንክ 339 ቢሊዮን ዶላር፣ ዓለማቀፍ የገንዘብ ተቋም 2.7 ቢሊዮን ዶላር፣ የቻይና መንግስት 1.4 ቢሊዮን ዶላር በየዓመቱ ለመስጠት ተስማምተው የነበረ ሲሆን እስካሁን አንዳቸውም ቃላቸውን መጠበቅ እንዳልቻሉ  ምንጮች  አመልክተዋል።
አበዳሪ ተቋማቱ በዋናነት ብድሩን ለመስጠት ያልፈቀዱት ላለመስጠት፣ ሃገሪቱ ከዚህ በፊት የነበረባት የብድር ጫና ከፍተኛ በመሆኑ፣ “ገንዘባችን አይመለስልንም” በሚል ስጋት ነው ተብሏል።
የአገሪቱ አጠቃላይ የውጭ ብድር ጫና 29 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን ይህም ከሃገሪቱ አጠቃላይ ምርት አንጻር የ27 በመቶ ድርሻን ይይዛል ተብሏል። ተቋማቱ ብድሩን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ግዙፍ ፋይናንስ የሚፈልጉ ፕሮጀክቶች ግንባታን እንደሚያዘገይና። የፋይናንስ እጥረትም እንዲጨምር እንደሚያደርግ ተነግሯል።

Read 10211 times