Monday, 23 August 2021 00:00

“የኔ ዘመን” የኪነ-ጥበብ ዝግጅት በአዳማ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ተቀማጭነቱን በአዳማ ከተማ ባደረገው “ተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድ ሁድ ካንሰር ኦርጋናይዜሽን የተዘጋጀውና ገቢው ሙሉ ለሙሉ በኦርጋናይዜሽኑ ለሚደገፉ የካንሰር ህሙማን ህፃናት መርጃ የሚውለው “የኔ ዘመን” የኪነ-ጥበብ ዝግጅት የፊታችን ሀሙስ ነሐሴ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ጀምሮ አዳማ በሚገኘው ኦሊያድ አዳራሽ  ይካሄዳል።
በዕለቱ ወግ፣ የኮሜዲ ስራ፣ አነቃቂ ንግግርና የህይወት ክህሎት አሰልጣኞች ንግግር የሚካሄድ ሲሆን፣ በዚህ መሰናዶ ላይ ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ፣ አሰልጣኞቹ  ሜሮን አበበ፣ ማንያዘዋል እሸቱ፣ ዳንኤል ወዳጄ፣ ስነወርቅ ታየ፣ በእምነት ደበበ፣ ነፃነት ዘነበና ሌሎችም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል። በዚህ የአሰልጣኞች የንግግርና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ ለመታደም መደበኛው የመግቢያ ዋጋ 100 ብር ሲሆን ቪአይፒው 300 ብር መሆኑም ተገልጿል። ህፃናቱንና የሚደግፋቸውን ማዕከል ለማገዝ በተሰናዳው በዚህ የኪነ-ጥበብ መሰናዶ ላይ በመታደም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አዘጋጆቹ ጋብዘዋል።

Read 11395 times