Print this page
Saturday, 28 August 2021 13:55

ከያኒ አድነው ወንድይራድ (አዶኒስ) ነገ ይዘከራ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

       “አዶኒስ” በተሰኘው የብዕር ስሙ የሚታወቀውና ከዛሬ ዓመት በፊት በሞት የተለየው አርክቴክት፣ ደራሲ፣ ተርጓሚና የሙዚቃ ባለሙያ አድነው ወንድራድ የሞተበትን አንደኛ ዓመትምክንያት በማድረግ ነገ ከረፋዱ 3፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይዘከራል።
በእለቱ የአዶኒስ ቤተሰቦች፣ የኪነ-ጥበብ ሰዎች ጥሪ የተደረገላላቸው  እንግዶች በመታሰቢያ መርሃግብሩ ላይ እንደሚታደሙ የመርሃ ግብሩ አዘጋጅ “ንባብ ለህይወት” መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቢንያም ከበደ ገልጸዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ አዶኒስ ስለሰራቸው ስራዎች፣ ስለ ህይወቱና እስኪያፍ ድረስ ስለነበረው እንቅስቃሴ ምስክርነት ይሰጣል።
የተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ሰራዎችም ይቀርባሉ ተብሏል። አዶኒስ ከአርክቴክትነት ሙያው ወደ ጥበቡ በገባ በአጭር ዓመታት ውስጥ በርካታ ከሰው ህሊና የማይጠፋ ስራዎችን የሰራ ሲሆን በመፅሀፍ “የአና ማስታወሻ” “አዶልፋ ኤክማን” እና “ፕሮፌሰሩ” የተሰኙትን ለንባብ ከማብቃቱም በተጨማሪ በርካታ ፅሁፎችና አጫጭር ልቦለዶችን ለንባብ አብቅቷል።
“ጣውንቶቹ”፣ “ክሊዮፓትራ”፣ “የአና ማስታወሻ”፣ “አጋምና ቁልቁል”፣ “ሞትና ትንሳኤ” በተሰኙ ቴአትሮቹ ህዝቡን ያስደመመው ከያኒው በኢትዮጵያ ቴሌቪዝን ለረጅም ዓመታት የታየውን “ገመና” ድራማን ከመፃፉም በተጨማሪ “መለከት” የተሰኘ እንደነ አንጋፋው ተዋናይ ፋቃዱ ተክለማርያም ያሉ እንቁዎች የተወኑበት የመጨረሻ ስራውንም እናስታውሳለን።
አዶኒስ የዛሬ ዓመት ነሀሴ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ነበር በድንገተኛ ህመም ህይወቱ ያለፈው።

Read 11389 times