Monday, 30 August 2021 00:00

“ለልጆች የሚያስፈልጉ 7 መሰረታዊ ፍላጎቶች” መፅሐፍ በድጋሚ ታተመ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)


          በደራሲ John.M. Drescher  የተፃፈውና በተርጓሚ ለገሰ ኩሳ “ለልጆች የሚያስፈልጉ ሰባት መሰረታዊ ፍላጎቶች” በሚል ወደ አማርኛ የተመለሰው ድንቅ የልጆች መፅሐፍ በድጋሚ ታትሞ ለንባብ በቃ።
የመፅሐፉ ደራሲ ጆን ኤም ደሬስቸር በልጆች አስተዳደግና ስነ-ልቦና ላይ የጠለቀ እውቀት ያለው ሲሆን መፅሐፉን በሚያዘጋጅበት ጊዜ ወላጆችን፣ ገጣሚያንን፣ የህግ ባለሙያዎችንና የሚመለከታቸውን ሁሉ አነጋገሮች ግብአት መውሰዱን ተርጓሚው በመፅሐፉ መግቢያ አስፍረዋል።
መፅሐፉ ወላጅ የሆነ ሁሉ ሊያነበው  የሚገባ እንደሆነ የገለጹት ተርጓሚው ለገሰ ኩሳ ለልጆች አስፈላጊ እንደሆኑ ልብ የማንላቸው ነገር ግን ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮች በውስጡ መያዙን አስታውሰው ሁሉም እንዲያነብና በእውቀት፣ በስነ-ምግባር የበለፀጉ አገር ተረካቢ ልጆችን ለማፍራት ቁልፍ ሚና እንዳው ተናግረዋል። በ152 ገፅ የተቀነበበው መፅሐፉ በ100 ብር ለገበያ ቀርቧል።



Read 9229 times