Saturday, 28 August 2021 14:42

ከፌስቡክ ገጾች በጨረፍታ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

      አሜሪካ ልክ ልካችንን ነገረችን!
                       ዘውድአለም ታደሠ


           (አማን መዝሙር)
አሜሪካ በኤምባሲዋ በኩል “ልካችሁን እወቁ” ብላናለች። «እናንት መናጢ ድሆች» ብላ ሰድባናለች። ወገን ተዋርደናል።
ሲያንቀለቅለን “USAID ለህዝቡ እያለ ጁንታውን ይቀልባል” ብለን ከሰን ነበር። ምነው አፋችንን በቆረጠው። አሜሪካ ዛሬ በፌስቡክ ገፅዋ አስገባችልን። (ኩሩው የጦቢያ ህዝብ ሆይ፤ ስድብህን እነሆ ወደ አማርኛ ተርጉሜልሀለሁ፡-)
«እናንት ንገሩኝ ባይ ችስቶች። እናንት ረሃብተኞች። ወልዳችሁ የትም የጣላችኋቸውን ድሆች ባበላን እጃችን አመድ አፋሽ ሆነ ማለት ነው? የኢትዮጵያን 7% ህዝብ የምንቀልበው እኛ መሆናችንን ምነው ረሳችሁት? በርግጥ ጁንታው ከምንወስደው ምግብ ላይ ሰርቆ ሊበላ ይችላል። እና ጁንታው ይበላል ተብሎ ህዝብ በረሃብ ይለቅ ወይ? እናንት ዘላለማችሁን ከጦርነት አትወጡ። ወይ ጠግባችሁ አትዋጉ። ዘላለማችሁን የኛ ሸክም ናችሁ። ሰው እናድርጋችሁ ብለው አውሮፓውያኑ በቅኝ ግዛት ቢይዟችሁ ነፃነት ይሻለናል ብላችሁ ገፋችኋቸው። ከዚያ እነሱ ሲለቋችሁ እርስ በርስ ትገዳደሉና የድል ቀን ታከብራላችሁ። ጦርነቱ ጋብ ሲልላችሁ ደግሞ ረሃብ ይገድላችኋል። ምን አፍ አለን ብላችሁ ነው ምታወሩት። ክፍት አፎች። በሐገራችሁ ሀፍረት የሚባል ነገር የለም ወይ? በማያገባን ገብተን 7 ፐርሰንቱን ድሃችሁን የምናበላው´ኮ ከፈጣሪ እናገኘዋለን ብለን ነው። እናንተ ግን ስንዴያችንን ጥርግ አርጋችሁ እየበላችሁ እኛኑ ሴጣን ታረጉናላችሁ። ወይ ነዳጅ ፣ ወይ አልማዝ በሌለው ደረቅ መሬት ምክኒያት ትዋጉና “አሜሪካኖች አዋጉን” ትላላችሁ። ለሃጢአታችሁ ሰይጣንን ለጠባችሁ ደግሞ አሜሪካን እስከ መቼ ሰበብ እያደረጋችሁ ትኖራላችሁ? ሼም የለም እንዴ?  ደግሞኮ እየሰደባችሁንም እርዳታችንን ትሻላችሁ። አልበዛም እንዴ? “እፀድቅ ብዬ ባዝላት ተንጠልጥላ ቀረች” አለች አሉ፤ ሂላሪ ክሊንተን»



Read 1553 times