Saturday, 04 September 2021 13:22

የኀፍረት ቁልፍ” ማክሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  “የኀፍረት ቁልፍ” የተሰኘው የደሳለኝ ስዩም መፅሐፍ የፊታችን ማክሰኞ  በ11 ሰዓት በኢትዮጵያ  ሆቴል ይመረቃል፡፡
በዕለቱም የመፅሀፉ ዳሰሳ እና ከመፅሀፉ ታሪክ የተወሰደ ተውኔት የሚቀርብ ሲሆን በምረቃ ሥነ ስነ-ስርዓቱ ላይ ሚካኤል ሽፈራው፣ ገጣሚ ዮሐንስ ምድሩ፣ ተዋናይ ግሩም ኤርሚያስ፣ የፊልም ባለሞያ ምስጋናው አጥናፉ፣ ደራሲ አያልነህ ሙላቱ፣ አርቲስት ንብረት ገላው፣ አርቲስት  ስዩም ተፈራ፣ ገጣሚ ዲበኩሉ ጌታ፣ ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀፀላ፣ አርቲስት  ደበበ እሸቱ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ አርቲስት ተስፋዬ ማሞ፣ አርቲስት ማህሌት ሰሎሞን፣ ደራሲ ህይወት እምሻው፣ ገጣሚ ዘላለም ምህረቱ፣ ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም ይገኛሉ። መፅሀፉ በዕለቱ ለሽያጭ የሚቀርብ ሲሆን መግቢያው በነፃ ነው ተብሏል፡፡

Read 16808 times