Print this page
Saturday, 04 September 2021 13:35

ወደ ትግራይ ሊሄድ የነበረው 1.6 ሚ. ሊትር ዘይት በሸማቾች ሊሸጥ ነው

Written by  መታሰቢያ ሳሣዬ
Rate this item
(4 votes)

ለትግራይ ህዝብ ኮታ ተመድቦ ከበላይነህ ክንዴ የዘይት ፋብሪካ ሰኔ 10 ቀን 2013 ተገዝቶ በጉና ንግድ ስራዎች መጋዘን ተከማችቶ የነበረው 1.6 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ደህንነቱ በመረጋገጡ በሸማቾች ሱቆች እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጠ።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ከትናንት በስቲያ በሰጠው ውሳኔ፤ ዘይቱ ደህንነቱ የተረጋገጠና የመጠቀሚያ ጊዜውም እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም ድረስ  የሚቆይ በመሆኑ በሸማቾች ሱቅ ተሸጦ ገንዘቡ በዝግ ሒሳብ እንዲቀመጥ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ባለፈው ሳምንት ፍ/ቤቱ የዘይቱ ደህንነት እንዲረጋገጥ ለኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ትዕዛዝ መስጠቱን መዘገባችን ይታወሳል።

Read 13620 times