Sunday, 12 September 2021 20:50

ኢትዮጵያዊው የጁ-ጂትሱና የጁዶ “ግራንድ ማስተር”

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(2 votes)

ኢትዮጵያዊው የጁ-ጂትሱና የጁዶ “ግራንድ ማስተር”
ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ
ልዩ ቃለምልልስ ካለፈው የቀጠለ
ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ ጉግሣ የፌዴራል ጀርመን የክብር መስቀል ኒሻን ተሸላሚ (Bearere of the Fedral Mereit of Cross) ናቸው፡፡ በአስተዳደር ማኔጅመንት ሁለተኛ ዲግሪ፣ በኢኮኖሚክስ የዶክትሬት ዲግሪ የያዙ ሲሆን በዳይምለር መርሴዲስ ቤንዝ የጀርመን ገበያ ዲቭዥን ውስጥ በሰው ሃይል ዲፓርትመንት የብዝሃነት እና የዘላቂ ልማት (Diversity & Sustainability) ማኔጀር ናቸው፡፡ በጁዶ እና ጁ-ጂትሱ ስፖርት ከ30 አመታት በላይ በመስራት 6ኛ ዳን ጥቁር ቀበቶ (ነጭ ቀይ) የግራንድ ማስተር Grand Master ማዕረግ ተቀዳጅተዋል፡፡ የአፍሪካ ጁ-ጂትሱ ፌዴሬሽን  ምክትል ፕሬዝዳንት ሲሆኑ፤ ከ2016 እኤአ ጀምሮ የዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ምክትል ፕሬዝዳንት እና  የዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን የዘላቂ ልማት (Sustainability & sport4climate) የበላይ ኃላፊ ሆነውም እያገለገሉ ናቸው፡፡
ዶክተር ፀጋዬ የህክምና ኦዲተር ከሆነችው ጀርመናዊቷ አኔት ጋር ጋብቻ ከመሰረቱ በኋላ ሁለት ሴት ልጆችን አፍርተዋል፡፡ ሊያን እና ሳሮን ይባላሉ፡፡ ሳሮን በጀርመን ፊልም መድረክ ወጣት ተዋናይ ስትሆን ከአፍጋኒስታን የመጣች ስደተኛ ቦክሰኛ ሆና የተወነችበት የቴሌቭዥን ፊልም ጥቅምት 1/2021 በጀርመን ብሔራዊ ቲቪ መታየት ይጀምራል፡፡


በስፖርቱ፤ በዲፕሎማሲውና በበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ያገኟቸው ስኬቶች የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን ገፅታ በመገንባት ምን  አስተዋጽዖ ይኖራቸዋል?
ብዙዎች እንደምታውቁት ከጀርመን ፕሬዝዳንት ‹‹የፌደራሉን ከፍተኛ የመስቀል ኒሻን›› the Federal Cross of Merit of the Federal Republic of Germany መቀበሌ ታላቅ  ክብርና ደስታን አጎናፅፎኛል። ለጀርመን፣ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ህዝልዩ ቃለምልልስ ካለፈው የቀጠለ
ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ ጉግሣ የፌዴራል ጀርመን የክብር መስቀል ኒሻን ተሸላሚ (Bearere of the Fedral Mereit of Cross) ናቸው፡፡ በአስተዳደር ማኔጅመንት ሁለተኛ ዲግሪ፣ በኢኮኖሚክስ የዶክትሬት ዲግሪ የያዙ ሲሆን በዳይምለር መርሴዲስ ቤንዝ የጀርመን ገበያ ዲቭዥን ውስጥ በሰው ሃይል ዲፓርትመንት የብዝሃነት እና የዘላቂ ልማት (Diversity & Sustainability) ማኔጀር ናቸው፡፡ በጁዶ እና ጁ-ጂትሱ ስፖርት ከ30 አመታት በላይ በመስራት 6ኛ ዳን ጥቁር ቀበቶ (ነጭ ቀይ) የግራንድ ማስተር Grand Master ማዕረግ ተቀዳጅተዋል፡፡ የአፍሪካ ጁ-ጂትሱ ፌዴሬሽን  ምክትል ፕሬዝዳንት ሲሆኑ፤ ከ2016 እኤአ ጀምሮ የዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ምክትል ፕሬዝዳንት እና  የዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን የዘላቂ ልማት (Sustainability & sport4climate) የበላይ ኃላፊ ሆነውም እያገለገሉ ናቸው፡፡
ዶክተር ፀጋዬ የህክምና ኦዲተር ከሆነችው ጀርመናዊቷ አኔት ጋር ጋብቻ ከመሰረቱ በኋላ ሁለት ሴት ልጆችን አፍርተዋል፡፡ ሊያን እና ሳሮን ይባላሉ፡፡ ሳሮን በጀርመን ፊልም መድረክ ወጣት ተዋናይ ስትሆን ከአፍጋኒስታን የመጣች ስደተኛ ቦክሰኛ ሆና የተወነችበት የቴሌቭዥን ፊልም ጥቅምት 1/2021 በጀርመን ብሔራዊ ቲቪ መታየት ይጀምራል፡፡
ቦች ከልማት ግብ ጋር ተያይዞ የገባሁት ቃል ኪዳን በመተግበር ይህን ልዩ ክብር ተሸልሚያለሁ። በስፖርትም በኩል   ለሰላም፣ ፍትሃዊነት፣ ትምህርት እና እሴት በማስተላለፍ ብዙ አስተዋፅኦ አበርክቻለሁ፡፡  
የመስቀል ኒሻኑን ከተቀበልኩ ከሁለት ወራት በኋላ ደግሞ በጀርመን ፌዴሬሽን አማካኝነት የግራንድ ማስተር ማዕረግ  አግኝቻለሁ፡፡ ምናልባትም ከዚህ በፊት በጀርመን የሚኖር ሌላ አፍሪቃዊ ያላገኘው ክብር ይመስለኛል። ከእነዚህ የክብር ሽልማቶች ጋር በተገናኘ ቀድሞ የሚጠራው ስሜ ሳይሆን ከየት  አገር እንደመጣሁ ነው - ከኢትዮጵያ።  ከጀርመን እና ከኢትዮጵያ የተሰማቸውን ኩራትና ደስታ የሚገልፁ ብዙ መልዕክቶች ደርሰውኛል። ስለ  ኢትዮጵያ በጎ ገፅታዋ የተነሳበት፣ ስለ ሕዝባዊ ዲፕሎማሲ ዋጋ የተሰጠበት ስኬት ነው፡፡  በበጎ ፈቃደኝነት ለሰው ልጆች የበለጠ አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚፈልጉን ሁሉ የሚያነሳሳ እና ብዙ ደጋፊዎችን የሚገኝበት ነው። እኛ ኢትዮጵያውያን ሌሎች የሚገኙበት  ደረጃ ላይ የምንደርስበትን አቅም  ያሳያል።  ስለዚህም ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የተሰጠ ሽልማት  እንደሆነ አምናለሁ።
በ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን የነበራትን ተሳትፎና ተያያዥ ሁኔታዎችን በተመለከተ ምን ታዝበዋል?
የተለዩ እይታዎች መግለፅ እፈልጋለሁ። በመጀመርያ ደረጃ የኢትዮጵያ ቡድን የነበረው ውጤት ያልተጠበቀና አሳዛኝ ነበር። ብዙ ተስፋ መቁረጥና ብስጭት አስተውያለሁ። በአመዛኙ ስፖርቱን ከሚመራው የአስተዳደር ሥርዓት እንደሚገናኝ ይሰማኛል፤ የስፖርት አስተዳደሩን በባለሙያ  እንደገና ማደራጀት ያስፈልጋል። በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያውያንም ለሌሎች አገራት ዜግነት የቀየሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያስመዘገቧቸውን ውጤቶችም በአድናቆት ነው የምመለከተው፡፡ ኢትዮጵያ የሚለው ስም በሁሉም ሰው አእምሮ ሲንቃጨል ነበር። ይህም ከአትሌቶቹ ስኬት ውጪ ስፖርቱን የሚያስተዳድረው መዋቅር ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ ያሳያል፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች ደጋግሜ እንደጠቀስኩት ኢትዮጵያ ላይ ሁለት ዜግነት እንዲኖር መፍቀድ በጣም ያስፈልጋል፡፡ በዓለም ዙርያ 120 አገራትና በጎረቤታችን ኬንያ ተግባራዊ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡  
በኦሎምፒኩ ወቅት ጃፓን ውስጥ የነበረውን አስከፊ የአየር ጠባይም በተጨማሪ ማንሳት የሚያስፈልግ ሲሆን ለረጅም ርቀት ሩጫዎች ተስማሚ አለመሆኑን መዘንጋት አልነበረበትም።  ጃፓን በዚህ ምክንያት ከፍተኛ ትችት ደርሶባታል። ኦሎምፒኩ ላይ በወቅቱ በረሃ መሰል የአየር ጠባይ እንዳለ አስቀድመን ብናውቅ ኖሮ የኢትዮጵያን አትሌቶች በኢትዮጵያ ሞቃታማ አካባቢዎች በማሰልጠን መስራት ነበረብን።
ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ፌዴሬሽኖች ቢኖሩንም  በጣም ጥቂት በሆኑ የስፖርት ዓይነቶች ነው የተሳተፍነው፡፡ በበርካታ ስፖርቶች አትሌቶችን መላክ አለመቻሏንም በቁጭት ነው የታዘብኩት። ታላቁ አበበ ቢቂላ በፓራሊምፒክ ላይ በቀስት ውርወራ ተሳታፊ እንደነበር አስታውሳለሁ። ይህ አይነቱ ተመክሮ ሊኖረን ይገባ ነበር፡፡
በእኛ ስፖርት ጁዶ እንኳን (ጁዶ እና ጁ-ጂትሱ ከነፃ ትግል  እና ከግሪኮችና ሮማዎች ፍልሚያ ጋር ይመሳሰላል) የምንሳተፍበት እድል ልናገኝ እንችል ነበር። ያልተቻለበት ምክንያትም  የሚያሳዝን ነው፡፡  በፌዴራል ስፖርት ማዕቀፍ ውስጥ ሆነን ፌዴሬሽኑን ለማቋቋም አስቸጋሪ ነበር። በእኔ አመለካከት በስፖርቱ አስተዳደር ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት በጣም ጥብቅ የሆኑ ሁኔታዎች በሌሎች የዓለም ሀገራትም የሚገኝ አይመስለኝም።  አዲስ ስፖርት ወይም ክለብ  ማቋቋም ለምን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚያስቸግር አይገባኝም፡፡  የስፖርት ባለስልጣናት ከዚህ በፊት ለልዩ ስፖርቶች  የሰጡትን እድል በሌላው ለመተግበር አለመቻላቸው እስካሁን አልገባኝም።
በነገራችን ላይ የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አቃቤ ንዋይ እና የቡድን መሪ የነበረች ኢትዮጵያዊት  በኦሎምፒኩ መክፈቻ ላይ ሰንደቅ አላማውን ይዛ በመሰለፏ ከአየአቅጣጫው በተሰጡት አስተያየቶችም መደንገጤን ለመግለፅ እፈልጋለሀሁ፡፡ በወቅቱ የቀረቡት ትችቶች በዜግነት ላይ ያነጣጠሩ መሆናቸው ህገወጥ እና አሳፋሪ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎችን በትውልድ አገራችው የተለያዩ መብቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በ1994 እ.ኢ.አ. የወጣ አዋጅ አለ፡፡ በዚህ አዋጅ መሰረት በሀገሪቱ ፓርላማ ለመመረጥና በወታደራዊ፣ በፖሊስና በፀጥታ ኃይሎች ውስጥ በመደበኛ ደረጃ የማገልገል መብት በስተቀር ሌሎች የኢትዮጵያ ዜጎች ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ መታወቅ ነበረበት። “ኢትዮጵያ ለምን በእንግሊዛዊ ተወከለች” የሚሉ አስተያየቶችን መስማት ትክክል አልነበረም፡፡ ይህ የኢትዮጵያዊነትን አዋጅ የሚጥስ ከመሆኑም በላይ ለኢትዮጵያ ደህንነት ገንዘብ በመደገፍ፣ ዕውቀትን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ “ኢትዮጵያውያን” ብቻ እንደሆኑ አድርገው በማዋጣትና በማካፈል በትጋት የሚሰሩ በርካታ ዲያስፖራዎችን መልካም ስም ማጥፋት ነው።
በኢትዮጵያ ስፖርት አስተዳደርና አመራር ዙርያ የሚያነሷቸው ሃሳቦች ካሉ?
የኢትዮጵያ ስፖርት በማያቋርጥ መዋቅራዊ ለውጦች ውስጥ መሆኑን አስተውያለሁ። በአንድ በኩል ይህ ጥሩ የዕድገት ምልክት  ቢሆንም በሃላፊነት ላይ የሚቀመጡ ሰዎች መቀያየራቸውና ደንቦች በየጊዜው የሚለዋወጡ መሆናቸው በስፖርቱ ቀጣይነት ላይ  ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከጀርመን ያገኘኋቸውን ተሞክሮዎችን በማካፈል ተሳትፎ አድርጌያለሁ። በ2019 እኤአ ለፌደራሉ የስፖርት ኮሚሽን፣ ለአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽንና የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ዳይሬክተሮች ዎርክሾፖችን ሰጥቻለሁ፡፡   ስፖርትን ጨምሮ ከጀርመን የሚገኙ ተግባራዊ የዕውቀት ዝውውሮችን የተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ በማዘጋጀት  ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትም አቅርቢያለሁ።
በኢትዮጵያ የስፖርት አወቃቀርና ፌዴሬሽኖች ላይ ከጀርመን አኳያ ጽሑፎችን በማቅረብ ለኢትዮጵያ የስፖርት ሕግ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ፈጥርያለሁ፡፡ የጀርመንን ልምድ በመጠቀም  በኢትዮጵያ ስታዲየሞች ውስጥ የሚፈፀመውን ስርዓት አልበኝነትን ለመከላከልና ለማስቀረት የሚያግዝ ምክረ ሃሳብም ሰጥቻለሁ፡፡ የኢትዮጵያን የስፖርት ፖሊሲ የሚያሻሽሉ  አንዳንድ ሀሳቦችንም አቅርቤያለሁ።
በተለያዩ ግዜያት ካቀረብኳቸው ምክረ ሃሳቦችና ጥናታዊ ፅሁፎች መካከል አንዳንዶቹ ተቀባይነት ማግኘታቸው አስደስቶኛል። በአጠቃላይ በአስተዳደራዊ ጥራት ላይ ማተኮር እና ስፖርቱ በባለሙያዎች መመራቱ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም ማለት ለምሳሌ ስፖርቱን የሚመሩ ባለስልጣናት በጁዶ እና በጁ ጂትሱ ስፖርት ላይ ከመወሰናቸው በፊት አስቀድመው እኔን ባለሙያውን ሊጠይቁኝ ይገባል። ከስፖርቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ወይም ምንም ሃሳብ የሌላቸው ሰዎችን በማማከር መወሰን የለባቸውም።  ይህም ለሁሉም የስፖርት ባለሙያዎችም መስራት ይኖርበታል፡፡ ከባለሙያዎች ጋር መስራት ወይም ኃላፊነቱን መስጠት ያስፈልጋል። ስፖርቱን የሚያስተዳድሩ ባለስልጣናት አደረጃጀታቸውን፤ መዋቅራቸውን ማሻሻል አለባቸው። ዛሬም ድረስ  በጥራት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ብዛትን ባነጣጠረ  የሶሻሊዝም ስርዓት ስፖርቱ የተዘፈቀ ይመስላል። በተጨማሪም ትኩረቱ በግለሰብ ላይ ሳይሆን በደንቡ ላይ መሆን ይኖርበታል ። በኢትዮጵያ ስፖርት የሚተዳደረው በመመርያ እንጅ በስፖርት አዋጅ ወይም ሕግ አይደለም።
ኃላፊነቶችን በግልጽ የሚመድብ፣ የስፖርት ቅሬታን የሚፈታ፣ ድርጅቶችን እንዴት ማስተዳደር እና በጀት ማውጣት እንደሚቻል ሕጋዊ የሚያደርግ ግልጽ የስፖርት ሕግ እንዲኖር ተስፋ አደርጋለሁ። በነገራችን ላይ በጀት መስጠት ማለት በበጀት ለጋሹ (መንግስት) ኦዲትና አፈጻጸም ቁጥጥር ማድረግ/መቀበል ማለት ነው። ይህ ካልሆነ ግን ወደፊት ብዙም ስፖርቱን የምናሻሻልበት እድል አይታየኝም። እንደ “ዳያስፖራ” ኢትዮጵያዊነቴ የኔን ፈታኝ መንገድ ሌሎች እንዲከተሉ መምከርም ያስቸግረኛል።
 ለወደፊቱ ዕቅድዎ ምንድነው?
ለውጥ ለማምጣት፣ የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል እና ለጥራት አስተዋጽኦ ለማበርከት እና ፈተናዎችን እንደ እድል ለመመልከት ነው የምፈልገው፡፡ ማንዴላ እንደተናገሩት፥ “እስኪደረስ  ሁልጊዜ የማይቻል ይመስላል። “It always seems impossible until you make it.  በሙያዬ ያካበትኩት የበሰለ ልምድ እና ያዳበርኳቸው ዝንባሌዎች ያሰብኩትን ለመተግበር ያስችለኛል። ሌላው ነጥብ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙሃኑን ያቀፉትንና ዕውቀትን በፍጥነት ለመቅሰምና ለመማር ዝግጁ የሆኑትን ወጣቶች መደገፍ ነው። የተሳሳተ ጎዳና እንዳይከተሉ የእኛ ድጋፍና ተሞክሮ ያስፈልጋቸዋል ።
የአዲስ ዓመት መልካም ምኞትዎ…
ለኢትዮጵያ እና ለተከበሩ ወገኖቼ ኢትዮጵያውያን መጪው 2014 የሰላም፣ የእርቅ እና የመግባባት፣ የኑሮ ውድነት የሚቀንስበት፣ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ የሚገታበት፣ ለአገራችን፣ ለጤንነታችን እና ለስፖርት ትርጉም የምንስጥበት በተጨማሪም ቀናነት፣ እንድነት እና መከባበርን መፈቃቀርን የሚያመጣ  ዘመን እመኛለሁ።


Read 9581 times Last modified on Monday, 13 September 2021 10:33