በደራሲና ጋዜጠኛ ሲሞን ሪቭ `one day in septmeber` በሚል ርዕስና በእውቁ ተርጓሚና ደራሲ ጥላሁን ግርማ አንጎ “ከሙኒክ ባሻገር” በሚል ወደ አማርኛ የተመለሰው አዲስ መፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ። መጽሐፉ በዋናነት በ1972 በሙኒክ ኦሎምፒክ በጥቁሩ መስከረም” የአሸባሪው ቡድን የተፈፀመውን ግድያና የእስራኤል የበቀል ዘመቻ የሆነውን “መቅሰፍተ-ኤል” ሙሉ ታሪክ ሰንዶ የያዘ ስለመሆኑ ተርጓሚው ገልጿል፡፡
መፅሀፉ መነሻውን በሙኒክ ኦሎምፒክ የተፈፀመውን ግድያና ሽብር ያድርግ እንጂ አጠቃላይ የሽብርተኝነን አስከፊነት፣ በሽብር ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ስቃይ፣ የቤተሰቦቻቸውን በሀዘን መሰበርና አጠቃላይ ህመሙን ያስቃኛል ተብሏል። በ493 ገፅ የተቀነበበው መፅሐፉ በ350 ብርና በ40 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡
ደራሲና ተርጓሚ ጥላሁን ግርማ አንጎ ከዚህ ቀደም የእውቁን ደቡብ አፍሪካዊ ኮሜዲያን ትሬቨርነዋህን ታሪክ የሚያስቃኘውን `born a crime` መፅሐፍ “የአመጻ ልጅ” በሚል ከመተርጎሙም ባሻገር 13 ደራሲያን በተሳተፉበት “አቦል” መጽሐፍ ላይ “የምርቃቱ መጽሄት” የተሰኘ አጭር ልቦለድና “በካልካታ ጎዳና” የተሰኘ አጭር ትርጉም ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል