Friday, 01 October 2021 00:00

ቢጂአይ ኢትዮጵያ ለተፈናቃዮች ከ3 ሚ. ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በሃገራችን የሰሜኑ ክፍል የትህነግ ሃይሎች በከፈቱት ጦርነት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በሰሜን ወሎ ኮምቦልቻ ለተጠለሉ ከ16 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች  ቢጂአይ ኢትዮጵያ የኮምቦልቻ ቢራ ፋብሪካ ሰራተኞችና ፋብሪካው ከ3.2 ሚሊዮን ብር በላይ ለገሱ። በቢጂአይ ኢትዮጵያ የኮምቦልቻ ቢራ ፋብሪካ ሰራተኞች፤ “እኛ እያለን የሰሜን ወሎ ወገኖች አይራቡም” በማለት ከደሞዛቸው ያዋጡትን 2 ሚ265 ሺህ 552 ብር የለገሱ ሲሆን፣ ቢጂአይ ኢትዮጵያ በበኩሉ፤ 1ሚ ብር የሚያወጡ ብርድ ልብሶች ለግሷል።
 በኮምቦልቻ ከተማ ሸሻ በር አንደኛ ደረጃና የጎፍ አንደኛ ደረጃ ት_ቤቶችን ጨምሮ በ8 የመንግስት ት_ቤቶችና በዘጠኝ የተለያዩ የግለሰብ የተጀመሩ ህንፃዎች ውስጥ በድምሩ በ17 መጠለያዎች ከ16 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች መኖራቸውን የገለፁት ም_ከንቲባው ኢ_ር አህመድ የሱፍ፣ የተፈናቃዮቹ ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መምጣቱንም ጠቁመዋል።
  እስካሁን ባለው ሁኔታ በኮምቦልቻ ላሉ ተፈናቃዮች ከከተማው ህዝብም ሆነ ከእርዳታ ሰጪዎች አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የተናገሩት ም/ከንቲባው፣ የተፈናቃዩ ቁጥር እየጨመረ ቢሄድ ምን መደረግ አለበት በሚለው ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ  መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።
 በቅርብ ቀን ትምህርት እንደሚጀመር በማስታወስ ለተፈናቆቹን የተዘጋጀ ሌላ መጠለያ ስለመኖሩ የጠየቅናቸው ም/ከንቲባው ጉዳዩን ታሳቢ በማድረግ ተለዋጭ መጠለያዎችን ማዘጋጀታቸውንና ምቹ በማድረግ ተፈናቃዮቹ ወደ ተዘጋጀው መጠለያ በማዛወር ትH;T| ቤቶቹ ለትምህርት ዝግጁ እንደሚሆኑ አብራርተዋል።
ቢጂአይ ኢትዮጵያ በአገራችን ለሚከሰቱ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ፈጥኖ ምላሽ በመስጠት ግንባር ቀደም የሆነ ህዝባዊ የንግድ ድርጅት መሆኑን የገለፁት የቢጂአይ ኢትዮጵያ ሃላፊዎች፤ አሁንም ፋብሪካውና የፋብሪካው ሰራተኞች በመተባበር ለሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች ከሶስት ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ገልፀው ድጋፉ በጎንደርም እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
 በኮምቦልቻ የሚገኙት አብዛኞቹ ተፈናቃዮች ሴቶችና ህፃናት ሲሆኑ አብዛኞቹ ባሎቻቸው ታላላቅ ልጆቻቸውና አባቶቻቸው ትህነግን ለመመከት ከሰራዊቱ ጋር ግንባር ላይ እንደሆኑ ነግረውናል። ተፈናቃዮቹ የኮምቦልቻ ህዝብ እያደረገላቸው ላለው ድጋፍና እያሳያቸው ላለው ርህራሄ  በእጅጉ አመስግነዋል።


Read 11925 times