Sunday, 03 October 2021 18:26

አባባሎች

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 የአዲስ አበባ የትራፊክ አደጋ
ግኝቶች - በ2013
በ2013 ዓ.ም በትራፊክ  አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ2012 ጋር ሲነፃፀር፣ በ13 በመቶ ቀንሷል፤ በዚህም የ58 ሰዎች ህይወትን መታደግ ተችሏል፡፡
በዚሁ በጀት ዓመት በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን ካጡ አጠቃላይ የመንገድ ተጠቃሚዎች መካከል 83 በመቶ (3/4) የሚሆኑት እግረኞች ሲሆኑ አደጋው የተከሰተውም በተለይ መንገድ በሚሻገሩ ወቅት ነው፡፡
በዓመቱ 87 በመቶ ያህሉ የትራፊክ አደጋ ሞት ተጠቂዎች ወንዶች ነበሩ፡፡
ግማሽ ያህሉ የትራፊክ አደጋ ሞት የተከሰተው ከ30 እስከ 59 ዕድሜ ክልል ውስጥ ነው፡፡
ከፍተኛው የትራፊክ አደጋ የሞት ቁጥር የተከሰተው ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት ነው፡፡
ከፍተኛው የትራፊክ አደጋ የሞት ቁጥር የተከሰተው በሚያዝያ ወርና በአርብ ቀን ነው፡፡
75 በመቶ የሚሆነው የአካል ጉዳት የደረሰው በወንዶች ላይ ነው፡፡
(ምንጭ፡- በአዲስ አበባ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ)


Read 1087 times