Saturday, 09 October 2021 00:00

ሃይኒከን ኢትዮጵያ፤ የጀምስ ቦንድ ፊልም አቀረበ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 የታዋቂው የፊልም ባለሙያ  ዳንኤል ክሬግ ወይም ጀምስ ቦንድ የመጨረሻ ፊልም እንደሆነ የተነገረለት “No time to die” የተሰኘውን አዲስ ፊልም፣ ሃይኒከን ኢትዮጵያ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያ ፊልም አፍቃሪያን  ለእይታ አበቃ።
ፊልሙ ትናንት በሸራተን አዲስ በተከናወነ የቀይ ምንጣፍ ሥነሥርዓት ዝነኛ አርቲስቶችና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት  ታይቷል፡፡
የአገራችንን የእግር ኳስ አፍቃሪያን ፍላጎት ለማርካት የሻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫና እነ ሮናልዲኒዮን የመሳሰሉ በዓለም ዝናቸው የናኘ ተጫዋቾች ወደ ኢትዮጵያ በማመጣት የሚታወቀው ሃይንከን ኢትዮጵያ፤ አሁን ደግሞ በመላው ዓለም እጅግ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኘውን “No time to die” የተሰኘ የጀምስ ቦንድ አዲስ ፊልም ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ለፊልም አፍቃሪያኑ አቅርቧል።
ሃይንከን ኢትዮጵያ፤ የፊልም አፍቃርያንን ፍላጎት ለማርካትና ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ቤተሰባዊ ቅርርብ ይበልጥ ለማጠናከር በማሰብ፣ ፊልሙን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ለእይታ ማብቃቱ ታውቋል።
በሸራተን አዲስ በተከናወነው የቀይ ምንጣፍ ስነ-ስርዓት ላይ ታዋቂ ግለሰቦችን ጨምሮ የሃይኒከን ኢትዮጵያ ቤተሰቦችና የምርቱ ተጠቃሚዎች ታድመው ነበር፡፡ በእንግሊዝ በመጀመሪያ ቀን እይታ ብቻ ከ5 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ገቢ ማስገኘቱ የተነገረለትና ባለፈው ሳምንት በእንግሊዝና አየርላንድ በሚገኙ 772 ሲኒማ ቤቶች ውስጥ ለእይታ የበቃው አዲሱ የጀምስ ቦንድ “No time to die” ፊልም፤ በኤድናሞል ሲኒማና በጋስት ሲኒማ ለተመልካቾች እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ሃይኒከን፤ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ከጀምስ ቦንድ ፊልም ጋር ባለው የአጋርነት ስምምነት መሰረት ነው ፊልሙን ወደ ኢትዮጵያ ያስመጣው ተብሏል፡፡



Read 6564 times