Sunday, 17 October 2021 00:00

ጤናማ ሕዋሳት (Cell)ይራባሉ…ይሞታሉ፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(2 votes)

   አንድ ቤት ሲሰራ ብሎኬት ተደርድሮ ነው፡፡ የአንድ ሰው ሰውነት የሚገነባውም ልክ ቤት በሚገነባበት መልክ በህዋሳት ወይንም በCell ግንባታ አማካኝት ነው፡፡
 ዶ/ር ታደሰ ኡርጌ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት እና የመራቢያ አካላት ካንሰር ሕክምና Sub specialist (oncology gynecology)
ባለፉት ህትመቶቻችን የማህጸን ፍሬ ካንሰርን እንዲሁም ካንሰርን በሚመለከት የተለያዩ እማኝነቶ ችንና መረጃዎችን በማጣቀስ ካንሰር ከመከሰቱ አስቀድሞ መደረግ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች ለንባብ ብለናቸው ነበር፡፡ በዚህ እትም ደግሞ የሙ ያው ባለቤቶች በአሁኑ ሰአት ስላለው የካንሰር ሕመም ሁኔታ ምን ይላሉ? ለመሆኑ የኬሞቴራፒ እና የጨረር ሕክምና አሰጣጥ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል? ስንል ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ አቅንተን ዶ/ር ታደሰ ኡርጌን አነጋግረናል፡፡ ምላሻቸውን ታነቡ ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡
የካንሰር ሕመም ከየትኛውም የሰውነት ክፍል ሊነሳ ይችላል፡፡ በዋናነት ግን የሰውነት ህዋሳት ጤነኛ በሆነ መልኩ መራባት ሲገባቸው ጤናማ ባልሆነ መንገድ ሲራቡ ለካንሰር ሕመም ምክንያት ይሆናል፡፡ ጤናማ የሚባለው ሕዋሳት በተፈጥሮአቸው ይራባሉ ከዚያም ይሞታሉ፡፡ መራባታቸው አስፈላጊ ሲሆን ብቻ የሚራቡ ናቸው ማለት ነው፡፡ ግን ከካንሰር ጋር የሚያያዘው ሕዋሳት ምንም ማቆሚያ በሌለው መንገድ እየተራቡ እና እየጨመሩ መሄዳቸው ነው። እነዚህ ህዋሳት ሁሉም ሰውነት ውስጥ የሚኖሩ ናቸው፡፡ የማህ ጸን ጫፍ ካንሰር(cervical cancer) የዘር ፍሬ ካንሰር (Ovary cancere) ፤ከዋናው ማህጸን….ከታችኛው ማህጸን ክፍል…የሚነሱ የካንሰር አይነቶች አሉ፡፡ እንደማንኛውም ሰውነት ከእነዚህ አካላት ካንሰር ሊነሳ የሚችል ሲሆን ወይንም ደግሞ በዚያ ያሉ ህዋሳት ልንቆጣጠ ራቸው በማይቻል መንገድ ሊራቡ እና ወደሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሊሰራጩ፤ ሌሎች የሰውነት ክፍሎ ስራቸውን በትክክል እንዳይሰሩ ሊያደርጉዋቸው ይችላሉ፡፡ ከዚህም ባለፈ በስተመጨረ ሻው ህመሙ ወደከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ህመምተኛውን ለሞት የሚዳርጉበት ሁኔታ ሊከሰት ይችላል፡፡
የካንሰር ታካሚዎች ወደ ሕክምና የሚመጡበትን ጊዜ በሚመለከት በአብዛኛው ካንሰር ሕመሙ ሲጀምር ምልክት ስለሌለው ህመም ወደካንሰርነት ከመለወጡ በፊት ወደሐኪም ይቀርባሉ ለማለት አያስደፍርም፡፡ በእርግጥ የማህጸን በር ካንሰር የሚባለው ሕመም ወደካንሰርነት ከመለወጡ አስቀድሞ አንዳንድ ምልክቶችን ስለሚያሳይ ቶሎ ወደሕክምናው መግባት ይቻላል፡፡ የማህጸን በር ወይንም ጫፍ ካንሰር ካንሰር ከመሆኑ አስቀድሞ ቅድመ ካንሰር ምርመራ በማድረግ እና አስፈላጊውን ሕክምና በማድረግ ህመሙ ወደከፋ ደረጃ ሳይለወጥ ማዳን ይቻላል፡በሌላው አካል ላይ የሚከሰተው ካንሰር ግን አንዳንድ ምልክቶችን የሚያሳየው ህመሙ ወደ ካንሰር ከተለወጠ በሁዋላ ይሆናል ማለት ነው ዶ/ር ታደሰ እንደገለጹት፡፡
በማህጸን አካባቢ የሚኖረው ካንሰር ሕመም ምልክቶቹ የደም መፍሰስ፤አስቀድሞ የወር አበባው የቆመ ከሆነ እንደ የወር አበባ አይነት የደም ፍሰት የመሳሰሉት ይታያሉ፡፡ ይሄም ገና ሕመሙ በትንሽ ደረጃ ላይ እያለ የሚታይ ህመም ሲሆን እየቆየ ሲሄድ ግን ኢንፌክሽን የመፍጠር፤ ወደ ጎንና ወደጎን ባሉ የሰውት ክፍሎ ላይ የመሰራጨት፤እንዲሁም ጊዜ በተሰጠው ቁጥር ሩቅ ወደአሉ የሰውት ክፍሎችም ይሰራጫል፡፡ ስለዚህም ታካሚዎች ወደሆስፒታ ሊቀርቡ የሚችሉት ካንሰር በተለያየ ደረጃ ሲከሰት ነው ማለት ነው፡፡
የመዳን እድልን በሚመለከት ዶ/ር ታደሰ ያነሱት ነጥብ ታካሚዎች የካንሰር ሕመምን ምልክት ሊያዩ የሚችሉት የካንሰር ሴሉ በተለያየ ደረጃ ባለበት ሲሆን ታካሚዎች ለሚያዩት ምልክትም ደንገጥ ብለው በቶሎ ወደሕክምና አለመቅረባቸው ትልቁ ችግር ነው፡፡ በተለይም ቀለል ያሉትን ምልክቶች የመናቅ፤ ለሰው ሲያማክሩም አናንቆ በቀላሉ ሊድን የሚችል ነገር መሆኑን መንገር፤ ወደሕክምና በቀጥታ ከመሄድ ይልቅም ወደባህል ህክምና፤ ወደእምነት ቦታዎች በመሄድ በተለ ያዩ መንገዶች በሚያገኙዋቸው (እንደጸበል… እምት…. የብህል ቅጠላ ቅጠሎ… ስራስሮች…) በመሳሰሉት ነገሮች ይድናል በሚል እምነት መጉዋዝ በተለይም ከገጠር ለሚመጡ ታካሚዎች ትልቁ የመዘግየት ምክንያት ይሆናል፡፡ ህመሙ እየከፋ ሲሄድ ወደሕክምና ቢቀርቡም በፍጥነት ከሚርስ ጉዳት ከመታደግ ውጭ ማዳን የማይቻልበት ሁኔታ ሊያጋጥም ይችላል፡፡
ፈሳሽ በብዛት ማየት፤
የወር አበባ ከቆመ በሁዋላ ደም ማየት፤
ከወሲብ ግንኙነት በሁዋላ ደም ማየት፤
ሲታጠቡ ደም ማየት፤ካንሰሩ ገና በሽታ መሆን ሲጀምር የሚታዩ ምልክቶች ናቸው፡፡
በዚህ ደረጃ ብዙዎች ወደሕክምና የማይሄዱ ሲሆን ከላይ እንደተገለጸው በተለያየ ምክንያት ከተሰራጨ በሁዋላ ወደሕክምና ይቀርባሉ። ታካሚዎች የመዳን እድላቸው ምን ያህል ነው የሚለውን የሚወስነው የካንሰር ሕመሙ ምን ያህል ደረጃ ላይ ነው የሚለው ነው፡፡ለዚህም ምክንያቱ ሕዋሳቱ አለአግባብ መባዛት ከጀመሩ በሁዋላ እዚያው ከነበሩበት ቦታ የሚቆዩ ሳይሆን ወደሌላ ሰውነት መሰራጨታቸው ነው፡፡ ከዚያው ከተነሱበት ሰውነት ላይ ልሳሌም ከማህጸን ጫፍ ላይ ህዋሳቱ ሳይባዙ ከተያዙ ዝቅተኛ የሚባለው ሲሆን በኦፕራሲዮን ብቻ የመዳን እድሉ ሰፊ ነው፡፡ ችግሩ ግን በዚያ ደረጃ ላይ ላገኙ ስለሚችሉ ነው፡፡
ሕመምተኛው በዚህ ደረጃ ታክሞ ሊድን ይችላል የሚለውን ለመናገር መጀመሪያ ህዋሳቱ በሚ ታይም ሆነ በማይታይ መልኩ ከዚያው ከተፈጠሩበት ቦታ ላይ ናቸው ወይንስ ተስፋ ፍተዋል የሚለው ወሳኝ ነገር ነው፡፡ በአይን የሚታዩና የማይታዩ ሲባል በሰውነት በተለይም በማህጸን ጫፍ ዙሪያ ባሉ ንፊፊት በሚባሉት ወስጥ የካንሰር ሴሎቹ ከገቡ ከጊዜ በሁዋላ የመባዛት ነገር ይኖራቸዋል፡፡ ስለዚህ በኦፕራሲዮን ሕክምናው በአይን የሚታዩት ቢወገዱም እነዚዚያ በአይን የማይታዩት ደግሞ ከጊዜ በሁዋላ ስሚመለሱ የመዳን እድሉን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳሉ፡፡
የካንሰር ሕመምን የሚያስከትለው የህዋሳት አለአግባብ መባዛት መሆኑ ከላይ ተጠቅሶአል፡፡  የትኛውም የሰውነት አካል የእነዚህ ህዋሳት ጥርቅም ነው፡፡ ዝቅተኛው የሰውነት ደረጃ ህዋስ ወይንም Cell ነው፡፡ ልክ አንድ ቤት በሚሰራበት ወቅት ብሎኬት ተደርድሮ ቤት እንደሚሆን እንዲሁም የተለያዩ ክፍሎች ተሰርተውለት አንድ ህንጻ እንደሚገነባ ሁሉ ሰውነት የሚሰራውም Cell በሚባሉ ትናንሽ ብሎኬቶች ሲሆን እንዲሁም አንድ ቤት የተለያዩ ክፍሎች እንደሚኖሩት ሁሉ ሰውነትም በህዋሳት ተገንብቶ የተለያዩ አካላትን ይይዛል፡፡ ቤት ክፍሎቹን አሟልቶ አንድ ህንጻ እንደሚወጣው ሁሉ ሰውነትም በህዋስ ተገንብቶ የውስጥ አካላቱን ይዞ አንድ ሙሉ ሰው ይሆናል ማለት ነው ዶ/ር ታደሰ ኡርጌ እንዳብራሩት፡፡ ስለዚህም ህዋሳት ማለት ትንሹ የሰው ነት ክፍል ነው፡፡ ህዋሳት ጤናማ በሆነ ሁኔታ የሚባዙበት እንዲሁም መባዛት በማያስፈ ልግበት ወቅት መመባዛታቸው የሚቋረጥበት ሁኔታ ነው ትክክለኛው ተፈጥሮአዊ መንገድ፡፡ ካንሰር የሚባለው እነዚህ ህዋሳት ከቁጥጥር ውጭ በሆነ እና በህክምና ካልተገታ በቀር ማቆሚያ በሌለው መንገድ ሲባዙ ነው፡፡ የካንሰር ሕመሙ የሚገኝት የሰውነት ክፍል በዚያው ባለው ህዋስ አማካኝነት የሚፈጠር ሲሆን በእርግጥ ከሌላም የሰውት ክፍል የሚመጣት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡
ሰውነትን ሰውነት የሚያሰኙት ህዋሳት መባዛት በማይገባቸው ሁኔታ እንዲባዙና የካንሰር ሕመምን እንዲያስከትሉ ምክንያት የሚሆኑዋቸውን ነገሮች ዶ/ር ታደሰ ሲገልጹ ካንሰር እንዲከሰት ምክንያት የሚሆነው ምንድነው የሚለውን ለመፈተሸ መንገድ ይመራል ብለዋል፡፡ ካንሰር በብዙ ምክንያት የሚከሰት ሲሆን ቁርጥ ባለ መልስ ግን ለካንሰር ምክንያቱ ይህ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ካንሰር ከተወሰኑ የካንሰር አይነቶች በስተቀር የብዙ የጥርቅም ውጤት ነው፡
በዘር የሚተላለፍ የካንሰር ሕመም ስላለ ተፈጥሮ ለህመሙ መጋለጥ፤
የሴሎችን ተፈጥሮአዊ የመባዛት ሂደት የሚያበላሹ የአካባቢ ሁኔታዎች፤
የሰዎች የአኑዋኑዋር ሁኔታ(አመጋገብ….የመጠቀሚያ ሁኔታዎች.. ወዘተ የካንሰርን ሕመም ሊያስትሉ ይችላሉ፡፡
የተወሰኑ የካንሰር አይነቶች ግን ከላይ ከተጠቀሱት የሚለዩበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ ለምሳሌ የማህጸን ጫፍ ካንሰር የሚመጣው በቫይረስ ነው፡፡ HPV ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ለማህጸን በር ካንሰር ዋነኛ ምክንያቱ ነው፡፡ በእርግጥ ቫይረሱ እንደማንኛውም ቫይረስ የመተላለፊያ መንገድ ያለው ሲሆን በተለይም ከአኑዋኑዋር ሁኔታ ጋር የሚገናኝበት ከውጭ ወደ ሰውነት የሚመጣበት መንገድ ያለው ነው፡፡ በእርግጥ በቫይረሱ በመያዝ ብቻ ካንሰር ይመጣል ባይባልም ቫይረሱን ካንሰር እንዲያመጣ የሚያደርጉ ነገሮች አሉ፡፡ የ HPV ቫይረስ ኢንፌክሽን ከሌለ የካንሰር ህመም አይከሰትም ማለት ይቻላል፡፡

Read 10616 times