Sunday, 17 October 2021 00:00

ዳማት የሆቴልና ቢዝነስ ኮሌጅ ተማሪዎቹን አስመረቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 ዳማት የሆቴልና ቢዝነስ ኮሌጅ በሆቴልና ቢዝነስ ዘርፍ ያስተማራቸውን 650 ተማሪዎች ባለፈው ቅዳሜ በአምባሳደር ሲኒማ አስመረቀ፡፡ ከተመራቂዎቹ 300 ያህሉ በዲግሪ እንዲሁም 350ዎቹ ከደረጃ 1-4 ባለው የትምህርት መርሃ ግብር መመረቃቸውን የኮሌጁ ፕሬዝዳንት አቶ አንዷለም ተሾመ በእለቱ ተናግረዋል፡፡
በ2007 ዓ.ም ተመስርቶ ዘንድሮ ለ6ኛ ዙር የተማሪዎች ምረቃ የደረሰው ዳማት ኮሌጅ ባለፉት ሰባት ዓመታት በስድስት ዙሮች ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁን ፕሬዝዳንቱ ጨምረው ገልጸዋል፡፡  ዛሬ ለምረቃ ከበቁት ተማሪዎች መካከል 90 በመቶ ያህሉ ኮሌጁ ባዘጃገው የስራ ትስስር መሰረት የእድሉ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡ በዕለቱም ተማሪዎቹ የስራ ፈጠራ መነቃቃትና የራስ መተማመን እንዲያዳብሩ በአርቲስት የትናየት ታምሩና በሌሎችም የአነቃቂ ንግገሮቻቸው የሚታወቁ ግለሰቦች ባደረጉት አነቃቂ ንግግር ከነዚህ ተናጋሪዎች ልምድና ተሞክሮ እንዲቀስሙ ተደርጓል፡፡

Read 10595 times