Sunday, 17 October 2021 00:00

በእንግሊዙ ቤተ-መንግስት በአመት 17 የአደንዛዥ ዕጽ ወንጀሎች ተፈጽመዋል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

    ፖሊስ በቤተ-መንግስቱ በ12 ወራት 200 ወንጀሎች ተፈጽመዋል ብሏል

              የእንግሊዝ ፖሊስ በታላቁ የአገሪቱ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት ዌስትሚኒስተር ቅጽር ግቢ ውስጥ በ1 አመት ጊዜ ብቻ 17 የአደንዛዥ ዕጽ ወንጀሎች እንደተፈጸሙ ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡
የአገሪቱን ፖሊስ ጠቅሶ ዘጋርዲያን እንደዘገበው፣ እስካለፈው መጋቢት ወር በነበሩት 12 ወራት ውስጥ በዌስትሚኒስትር ቤተ-መንግስት ቅጽር ግቢ የአደንዛዥ ዕጽ ግብይት፣ አካላዊ ጥቃትና ስርቆትን ጨምሮ ከ200 በላይ የወንጀል ድርጊቶች ተፈጽመዋል፡፡
በቤተ-መንግስቱ ሁለት የአደንዛዥ ዕጽ አዘዋዋሪዎችና የተለያዩ አይነት አደንዛዥ ዕጾችን ይዘው የተገኙ 13 ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ የወንጀል ድርጊቶቹ የተፈጸሙት ከኮሮና ቫይረስ ገደቦች ጋር በተያያዘ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የፓርላማ አባላት እና ሰራተኞች ብቻ ቢሮ ይገቡ በነበረበት ጊዜ መሆኑ ጉዳዩን አነጋጋሪ ያደርገዋል ብሏል ዘገባው። በዌስትሚኒስትር እ.ኤ.አ ከ2016-2018 578 ያህል ወንጀሎች መፈጸማቸውን ስካይ ኒውስ ከሁለት አመታት በፊት ባወጣው ዘገባ ማስነበቡንም ዘገባው አስታውሷል፡፡



Read 2242 times