ውድ እግዚአብሄር፡- እንዴት እስካሁን አዲስ እንስሳትን አልፈጠርክም? ከኛ ጋር ያሉት የድሮዎቹ ብቻ ናቸውን።
ጆኒ
ውድ እግዚአብሄር፡- እግዚአብሄር መሆንህን እንዴት ነው ያወቅኸው?
ሳሚ
ውድ እግዚአብሄር፡- ወንድ አያቴ ትንሽ ልጅ እያለም፣ አንተ ነበርክ፡፡ ዕድሜህ ግን ስንት ነው?
ዴቭ
ውድ እግዚአብሄር፡- ማንም ከአንተ የተሻለ እግዚአብሄር ይሆናል ብዬ አላስብም። ይህን እንድታውቅልኝ እፈልጋለሁ። እንደዚህ የምለው ደሞ እግዚአብሄር ስለሆንክ ብቻ አይደለም፡፡
ቻርልስ
ውድ እግዚአብሄር፡- እውነት በአይን አትታይም ወይስ ስትደን ነው?
ሉሲ
ውድ እግዚአብሄር፡- ስቴፕለር ከታላላቆቹ ፈጠራዎችህ አንዱ ይመስለኛል።
ሩት ኤም
ውድ እግዚአብሄር፡- ለአንተ ከሚሰሩልህ ሰዎች ሁሉ ጴጥሮስና ዮሐንስን በጣም እወዳቸዋለው።
ሮዝ
ውድ እግዚአብሄር፡- አንዳንድ ነገሮች ከመፈጠራቸው በፊት ታውቃለህ እንዴ?
ቻርልስ