ለንባብ በቃ
በደራሲ ተዓምር ተ/ብርሃን የተሰናዳውና በተለያዩ ርዕስ ጉዳች የተፃፉ ልብወለድ ታሪኮችን የያዘ “ሞት ምቢና” ሌሎችም” የተሰኘ የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡
መፅሐፉ የተለያዩ ማህበራዊ ህይወቶችንና የህይወት ገፆቻችን ላይ የምንተገብራቸው ጉዳዮች በየርዕስ ርዕሱ ተሰንደው ተካተውበታል፡፡ 20 ያህል አጫጭር ታሪኮችን ባካተተው በዚህ መፅሐፍ ውስጥ የመፅሐፉን መጠሪያ ሞት,ምቢን ጨምሮ “ሚስ አማርኛ”፣ “ሱቅ በደረቴ”፣ “ትዳር”፣”ሀሜትና ፀጉር ቤት” “የአባቶች ታሪክ ላይ የቆመ ትውልድ” የሚሉና ሌሎችም ማህበራዊ ትዝብቶችን ይዟል፡፡ በ200 ገፅ የተቀነበበው ይሔው መፅሐፍ በ120 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
Saturday, 30 October 2021 00:00
“ሞት ምቢ እና ሌሎችም”
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና