Saturday, 06 November 2021 13:09

“የአምላክ ልጆች ፋውንዴሽን” ዛሬ ፕሮግራሞቹን ይፋ ያደርጋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

   የገቢ ማስባሰቢያ መርሃ ግብርም ያካሂዳል

               አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት የሆነው የአምላክ ልጆች ፋውንዴሽን ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በኢሰመኮ አዳራሽ ፕሮግራሞቹን ይፋ ያደርጋል። በዕለቱ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብርም ያከናውናል።
ገና በ10 ዓመቱ ራዕዩን ጽፎ ባስቀመጠውና በ23 ዓመት የወጣትነት አፍላ እድሜው ይህችን ዓለም በተሰናበተው ወጣት የአምለክ ፍቅር አለባቸው ስም የተቋቋመው “የአምላክ ልጆች ፋውንዴሽን” በዋናነት በልጆች አስተዳደግ፣ በቤተሰብ ግንባታ ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ልጆችን ህይወት በመቀየር እና ከቤተሰቦቻቸውና ከህብረተቡ ጋር በማቀላቀል ስራ ላይ የተሰማራ ሲሆን በበጎ አድራጎትና ማህበራት ኤጀንሲ በህጋዊ መንገድ የተቋቋመ ነው።
ወጣቱ የአምላክ ፍቅር አለባቸው ገና በ10 ዓመቱ (2001 ዓ.ም) ወላጅ አልባና የጎዳና ልጆችን ለመመገብ፣ ለማስተማርና ህይወታቸውን በዘላቂነት ለመቀየር እንዲሁም የሀገሩን ድህነት ለመቅረፍ የነበረውን ህልም በፅሁፍ  ጽፎ ያለፈ ሲሆን፣ የአምላክን ህልም ለማሳካት ቤተሰቦቹ በስሙ ፋውንዴሽን ያቋቋሙ ሲሆን ተቋሙ የወጣቱን ህልም ለማሳካት እንቅስቃሴ መጀመሩም ታውቋል። ዛሬ በሚካሄደው በዚህ መርሃ ግብር ወጣቱ የአምላክ ፍቅርን ከመዘከር ጀምሮ የፋውንዴሽኑ አላማና ተግባራት ለህዝብ የሚተዋወቁ ሲሆን የገቢ ማሰባሰቢያም እንደሚካሄድ ታውቋል። በእለቱ የአምላክ ወላጆች፣ ጓደኞች፣ የራዕዩ ደጋፊዎች ፣ የውጭና የአገር ውስጥ የፋውንዴሽኑ ድጋፍ ሰጪዎች በክብረ በዓሉ ላይ የሚታደሙ ሲሆን ሁሉም ይህን ፋውንዴሽን በሙያ፣ በእውቀትና በገንዘብ እንዲደግፍ ጥሪ ይተላለፋል ተብሏል።



Read 11420 times