Sunday, 07 November 2021 17:33

“ያላሻገረን ዴሞክራሲ” ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የደራሲ ምንተስኖት ጢቆ “ ያላሻገረን ዲሞክራሲ”  አዲስ መፅሐፍ ሰኞ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመፃሕፍትና ቤተመዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ (ወመዘክር) ይመረቃል።
በእለቱ የመፅሐፍ ዳሰሳ፣ ግጥም፣ ወግና የተመረጡ የመፅሐፉ ክፍሎች ለታዳሚ እንደሚቀርቡም ታውቋል። የመፅሐፉን ዳሰሳ አልማው ክፍሌ (ዶ/ር) እና የፍልስፍና ምሁሩ ዮናስ ዘውዴ የሚያቀርቡ ሲሆን መምህርት ዕፀገነት ከበደ ወግ እንደምታቀርብና ገጣሚያኑ ኤልያስ ሽታሁንና በቃ ሙሉ  የግጥም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉም ተብሏል። የታሪክ መምህሩ ቴዎድሮስ ዘርፉ መድረኩን የሚያጋረው ሲሆን በእለቱ በዚህ ጠቃሚ የመጽሐፍ ምረቃ ላይ ተገኝታችሁ ፋይዳ ያለው እውቀት እንድታገኙ ደራሲው ምንተስኖት ጢቆ ጋብዟል። “ያላሻገረን ዴሞክራሲ” መፅሐፍ የቀደመ የሀገራችንን ታሪክ መነሻ በማድግ የመጣንበት መንገድ ወደላቀ ዴሞክራሲና እድገት እንዴት እንዳላሻገረን፣ ያሉብንን ያካሄድና የስርዓት ህፀጾች እየነቀሰ መፍትሄ የሚያመለክት ነው ተብሏል። በ226 ገፅ የተቀነበበው መፅሐፉ በ250 ብርና በ25 ዶላር ለገበያ ቀርቧል።

Read 9583 times