Sunday, 07 November 2021 18:08

የስኬት ጥግ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

• ገንዘብ ለሁሉም ነገር መልስ ነው።
ሰሎሞን
• የገንዘብ እጦት የሁሉም ሃጢያቶች
ሥር ነው።
ጆርጅ በርናርድ ሾው
• ገንዘብ እወዳለሁ። ገንዘብም
ይወደኛል።
ሪቨረንድ አይክ
• ሃብታም የሚያደርግህ ደሞዝህ
አይደለም፤ የገንዘብ አወጣጥ ልማድህ
ነው።
ቻርልስ ኤ.ጃፌ
• ገንዘብ ደስታን ሊገዛልህ አይችልም፤
የበለጠ አስደሳች ዓይነት መከራን
ያመጣልሃል።
ስፓይክ ሚሊጋን
• ማንም ሰው ሌሎችን ካላበለፀገ በቀር
ራሱ አይበለጽግም።
አንድሪው ካርኒጄ
• ለገንዘብ የማትሰራበት ደረጃ ላይ
ትደርሳለህ።
ዋልት ዲዝኒ
• ሂሳብ አልወድም፤ ገንዘብ መቁጠር
ግን እወዳለሁ።
ያልታወቀ ሰው
• ከወጪ የተረፈህን አትቆጥብ፤
ከቁጠባ የተረፈህን ተጠቀም እንጂ።
ዋረን በፌ
• ገንዘብህን መቁጠር የምትችል ከሆነ፣ ተግተህ መሥራትህን ቀጥል።
ያልታወቀ ሰው
• ሃብት ህይወትን ሙሉ በሙሉ
የማጣጣም አቅም ነው።
ሔነሪ ዴቪድ ቶሮው
• ገንዘብ ሰዎችን አይለውጣቸውም፤
ይገልጣቸዋል እንጂ።
ያልታወቀ ሰው
• ባለጸጋ ለመሆን ተኝተህም ገንዘብ
መሥራት አለብህ።
ዴቪድ ቤይሌይ
• ገንዘብ ሁሉም ነገር አይደለም።
ዶሊ ፓርተን

Read 1039 times