Sunday, 07 November 2021 18:28

በመሪያቸው ላይ ያሟረቱ 30 ቱርካውያን ለፍርድ ሊቀርቡ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)



              የቱርኩ ፕሬዚዳንት ራሲብ ጣይብ ኤርዶጋን "ክፉኛ ታመዋል ካልሆነም ሞተዋል" የሚል ያልተጨበጠ መረጃ በትዊተር ማህበራዊ ሚዲያ በማሰራጨት በታላቁ መሪ ላይ አሟርተዋል የተባሉ 30 ቱርካውያን ክስ ሊመሰረትባቸው መሆኑን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
የአገሪቱን የደህንነት ቢሮ ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፣ ግለሰቦቹ ከዚህ በተጨማሪም የፕሬዚዳንት ኤርዶጋንን ክብር የሚነካና መልካም ሰብዕና የሚያጎድፉ መልዕክቶችን በማሰራጨት ምርመራ እየተደረገባቸው ሲሆን ክስ ለመመስረት አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡
የ67 አመቱ ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ከቀናት በፊት በተለቀቀ ቪዲዮ በአግባቡ ለመራመድ ሲቸገሩ መታየታቸውን ተከትሎ፣ በተለይ በማህበራዊ ድረገጾች የጤንነታቸውን ጉዳይ በተመለከተ ብዙ አጠራጣሪ ነገሮች በስፋት በመሰራጨት ላይ እንደሚገኝ የጠቆመው ዘገባው፤ የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች ግን ከንቱ አሉባልታ ነው መሪያችን ደህና ናቸው በማለት ሊያስተባብሉ መሞከራቸውንና "ከደህንነት ጋር በተያያዘ ነው" በሚል ኤርዶጋን በግላስኮው የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ሳይገኙ መቅረታቸው አሉባልታውን እንዳስፋፋውም አመልክቷል፡፡

Read 1529 times