Saturday, 20 November 2021 14:24

የመገናኛ መሳሪያዎች በእጃቸው የሚገኝ ግለሰቦችና ተቋማት በ15 ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ ቀረበ

Written by  መታሰቢያ ሳሣዬ
Rate this item
(1 Vote)

 ማንኛውም የኮሙዩኒኬሽን እና የመገናኛ መሳሪያዎች በእጃቸው የሚገኝ  ግለሰቦች እና ተቋማት በ15 ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግቡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አሳሰበ።
በኢትዮጵያ ህልዉና አደጋን ለመከላከል፣ ስጋት እና ሉአላዊነት ጥሰት ለመከላከል ሁሉን አቀፍ የጥንቃቄ እርምጃዎች መዉስድ አስፈላጊ መሆኑን የገለፀው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ  በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የኢንፎርሜሽን እና የኮሙዩኒኬሽን መሳሪያዎችን ሲመዘግብ እና ሲቆጣጠር የቆየ ቢሆንም አሁናዊ ይዞታን ለማወቅ እና እነዚህ የኮሚዩኒኬሽን መሳሪያዎች በአሸባሪዎች እና ገብረ-አበሮቻቸዉ ለሽብር አላማ እንዳይዉሉ መሳሪያዎቹን  እንደገና መመዝገብ እና በሚመለከተዉ አካል እጅ ስለመኖሩ ማወቅ ኤጀንሲዉ ተገቢ ሆኖ አግኝቶታል።
በመሆኑም የኮሙዩኒኬሽን እና የመገኛኛ መሳሪያዎች በእጁ የሚገኝ ማንኛዉም ግለሰብ፣ ተቋም፣ ኤምባሲ ወይም ዲፕሎማት፣ በመንግስታዊም ሆነ በግል ተቋማት ጥበቃ ላይ የተሰማሩ አካላት፣ በዘርፉ የተሰማሩ አስመጪዎች እና ላኪዎች በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እንዲያሳዉቁ አሳስቧል፡፡
በዚህም ወታደራዊ የቅኝት መሳሪያዎች ፣ወታደራዊ እና ሲቪል የመገናኛ መሳሪያዎች፣ቪሳት እና ቢጋንና ድሮኖች በግለሰቦች እጅ ወይም በተቋማት ውስጥ ሲጠቀም ያየ ማንኛዉም አካል ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በነጻ ስልክ ቁጥር 933 ወይም 0113851193 ፣ 0904049625 እና 0114701321 ማሳወቅ ይጠበቅበታል ነው የተባለው።

Read 10737 times