Saturday, 20 November 2021 14:28

ጅቡቲ “መሬቴ በኢትዮጵያ ላይ ለሚፈፀም ጥቃት መጠቀሚያ አይሆንም” አለች

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(5 votes)

 በኢትዮጵያ ላይ የውጭ ሃይሎች ጣልቃ ለመግባት የሚያደርጉትን ጥረት እንደምትቃወም  ያስታወቀችው ጅቡቲ፤ መሬቷም የአየር ክልሏም በጎረቤቶቿ ላይ ለሚደረግ ጣልቃ ገብነት መጠቀሚያ እንደማይውል አሳስባለች፡፡
በጅቡቲ የሚገኘው የአሜሪካ ጦር አዛዥ ከሰሞኑ “በኢትዮጵያ እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር ተያይዞ በአገሪቱ በተለይም በመዲናዋ ቀውስ የሚከሰት ከሆነ፣ የአሜሪካ ወታደሮች ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ለቢቢሲ መናገራቸውን ተከትሎ ነው የጅቡቲ መንግስት መግለጫውን የሰጠው፡፡
የጅቡቲ የወጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህመድ አሊ የሱፍ፤ “የጅቡቲ ግዛት በየትኛውም ጎረቤቶቻችን ላይ ለሚፈፀም ጥቃት መረማመጃ እንዲሆን ፈፅሞ አንፈቅድም” ብለዋል፡፡
 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃው ባጋሩት የመንግስታቸው  አቋም ላይ ጅቡቲ ከጎረቤቶቿ ጋር ጠንክራ ትስስር እንዳላት በማውሳት፤ ይህን ግንኙነት ትስስር የሚያበላሽን የትኛውንም የውጭ ሃይሎች ጣልቃ  ገብነት ፈፅሞ አንቀበልም እንደማትቀበል ገልፀዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ በኬኒያ ቆይታ ላደረጉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ያለምንም ጣልቃ ገብነት የራሷም የውስጥ ችግር የመፍታ አቅሙ እንዳላት የኬኒያ መንግስት ማስረዳቱን አስታውቋል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንም፤ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ግጭት አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሰው፣ በቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት አቢሲንጎ አማካይነት የሚደረገውን የማሸማገል ጥረት ሃገራቸው እንደምትደግፍ አስገንዝበዋል፡፡


Read 11711 times