Print this page
Saturday, 20 November 2021 14:48

“አፍሮ ፊገር” ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ማክሰኞ ያስመርቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   ከሁለት ዓመት በፊት የተቋቋመው አፍሮ ፊገር የሞደሊንግና የኪነ-ጥበብ ት/ቤት በሞዴሊንግ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በመጪው ማክሰኞ ህዳር 14 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ፡00 ጀምሮ በማርዮት ኢንተርናሽናል አፓርትመንት ሆቴል ያስመርቃል፡፡ ት/ቤቱ ዘንድሮ ተማሪዎቹን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያስመርቅ ሲሆን የሞዴሊንግ ሙያ እንደሌሎች ሞያዎች እንዲወደድ፣ እንዲከበር ለማደረግ ብሎም በዘርፉ ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት ታስቦ የተቋቋመ ት/ቤት እንደሆነ የአፍሮ ፊገር መስራችና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ዮሀንስ ገልፀዋል፡፡ በዕለቱ 60 ሴት እና 20 ወንድ በድምሩ 80 ሞዴሎች የሚመረቁ ሲሆን በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ በዘርፉ እውቅና ያላቸው ሞዴሎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙ አቶ አብርሃም ዩሃንስ ለአዲስ አድማስ  ጨምረው ገልፀዋል፡፡


Read 11339 times