Monday, 29 November 2021 00:00

የመጀመሪያዋ የስዊድን ጠ/ሚኒስትር ጧት ተሹመው ከሰዓት ስልጣን ለቀቁ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

   ባለፈው ረቡዕ ማለዳ በስዊድን ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ማግዳሊና አንደርሰን፣ ቃለ መሃላ ፈጽመው ስልጣን ከያዙ ከ7 ሰዓታት በኋላ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ እና ግሪን ፓርቲ የተባሉት ሁለት ዋነኛ የአገሪቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች በጥምረት መንግስት መመስረታቸውንና ማግዳሊና አንደርሰንም ባለፈው ረቡዕ በጠቅላይ ሚኒስትርነት መሾማቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ የሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ያቀረበው የበጀት ዕቅድ በፓርላማው ሊጸድቅ አለመቻሉንና ግሪን ፓርቲም ከሰዓት በኋላ ከጥምር መንግስቱ ራሱን ማግለሉን ተከትሎ፣ አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ህገ መንግስቱ በሚደነግገው መሰረት ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን አመልክቷል፡፡
ማግዳሊና አንደርሰን ፓርቲያቸው በቀጣይ ለብቻው መንግስት የሚመሰርት ከሆነ በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመስራት ፍላጎት እንዳላቸው መናገራቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ ሴትዮዋ ላለፉት ሰባት አመታት የስዊድን ገንዘብ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸውንም አስታውሷል፡፡

Read 2703 times