Saturday, 27 November 2021 14:46

“ታሪክ ምን ይለናል”

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የኪነ-ጥበብ መሰናዶ ዛሬ ይካሄዳል

        በሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት በየወሩ የሚካሄደው  የኪነጥበብ መሰናዶ የዚህ ወር ዝግጅት “ታሪክ ምን ይለናል” በሚል ርዕስ ዛሬ ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ይካሄዳል። በእለቱ ወግ፣ ዲስኩር፣ ግጥምና ሙዚቃ ለታዳሚ የሚቀርብ ሲሆን አብዛኛዎቹ ንግግሮች በአሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኩራሉም ተብሏል። በዝግጅቱ ላይ ዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ፣ ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ፣ ዶ/ር ሰምሐር ተክሌ፣ ደራሲና መምህር ታዬ ቦጋለ፣ ኮሜዲያን ሰመረ ካሳዬ (ባሪያው)፣ ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀጸላ፣ ገጣሚያኑ መንግስቱ ዘገዬ፣ በላይ በቀለ ወያ፣ ረድኤት ሞገስ፣ አስታውሰኝ ረጋሳና የህግ ባለሙያው ዳግማዊ አሰፋ ስራዎቻቸውን ከአድዋ ሙዚቃ ባንድ ጋር በመተባበር ያቀርባሉ ተብሏል። የመግቢያ ዋጋ 100 ብር ሲሆን፣ ትኬቶቹን በጃዕፈርና ዮናስ መፃህፍት መደብሮች ማግኘት እንደሚቻል ለማወቅ ተችሏል።

Read 11266 times