Saturday, 27 November 2021 14:48

“ፀሀዩ እንቁስላሴ ፀረ ፋሽስት አርበኛና የሀገር ባለውለታ” መፅሐፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የደራሲ አማረ ተግባሩ (ዶ/ር) “ፀሐዩ ዕንቁ ስላሴ ፀረ ፋሽሽት እርበኛና የሀገር ባለውለታ” መፅሐፍ ዛሬ ህዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ይመረቃል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጅግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ተገኝተው ንግግር የሚያደርጉ ሲሆን ደጃዝማች ወልደ ሰማያት ወልደ ገብርዔል በክብር እንግድነት እንደሚገኙና ትውስታቸውን እንደሚያካፍሉም ታውቋል፡፡ ደራሲ እንዳለ ጌታ ከበደ(ዶ/ር) በመፅሐፉ ላይ ደሰሳ የሚያቀርብ ሲሆን፣ደራሲ ይታገሱ ጌትነት ግጥም፣ ፀሐፊ ተውኔት ገጣሚና ደራሲ አያልነህ ሙላትና ከያኒ ጌትነት እንየው በባለታሪኩ አርበኛ ዙሪያ ምስክርነት እንደሚያቀርቡም ታውቋል፡፡ ጋዜጠኛ ሚካኤል አለማየሁ (የዕናኑ ልጅ) መድረኩን የሚያጋፍር ሲሆን፣ ደራሲው አማረ ተግባሩ (ዶ/ር) በመፅሀፋቸው ዙሪያ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 11249 times