Saturday, 27 November 2021 14:56

ኖቤል ይለኛል ‘ንዴ?!

Written by 
Rate this item
(7 votes)

ኢትዮጵያን ታክል ሃገር
በዙፋኗ ላይ ተሸሜ
የዚህን ህዝብ ቡራኬ
በምርቃት ተሸልሜ
ከሃድራው መሃል ከዝየራው
ከቱፋታው ታድሜ
ምን ክብር ይቀረኛልና ከእናቶች
ምርቃት እድሜ
ኢትዮጵያ ላይ ከመንገስ
ከጥቆሮች ቤተመቅደስ
እስቲ ምን የትስ አለ?
የጥህንን ክብር ያከለ?
ኖቤል ይለኛል ‘ንዴ?!
ከፀበሉ ተረጭጬ
ከወተቱ ተጎንጭጬ
በአናቴ ቅቤ ተቀብቼ
ከለምለም ሳር ተሰጥቼ
ቦኩ በአናቴ ሰክቼ
በርትቼ፣ረክቼ፣ወዝቼ
ቡልኮ ተከናንቤ
ካባ በጃኖ ደርቤ
በጋሞ ሽመና ጥበብ
በቀለማት ተንቆጥውቁጬ
በሃገሬ ጥለት ስሪት እዳር እዳር አጊጬ
የተሸለምኩትን ሽልማት ቁብ
ባትሉት ነው እንጂ
የእኛን ክብር ልክ ለመግለጥ
በሆነ ነበር እስረጂ
ኖቤል ይለኛል ‘ንዴ?!
አለም አክብሮ በሰጠኝ
በእርግጥ አልታበይም
ግና! ኢትዮጵያ ከሚል ስም በላይ
እመኘኝ ዝና አይገኝም
ሰንሰለት ከሆነ ማሰሪያ
የተሸለምኩት ሽልማት
ያውልኽ! ውሰደው ወዲያ
ለሚገዛልህ ጣልለት
እኔን እንኳን በኖቤል
በማዕበል አታቆመኝም
ባርነት ‘ኮ አላውቅም
ነፃነት ነው የወለደኝ
እምቢኝ! ሀገሬን አልተውም
ሎሬት ብለህ አትደልለኝ
ፍልሚያ አለብኝ አንተ
ሰው ይልቅ ዞር በልልኝ
ወጥመድ ከሆ የተሰጠኝ
“ፕራይዝክን” ውሰድልኝ
ኖቤል ይለኛል ‘ንዴ?!
(ከጌታቸው ኅሩይ ገፅ የተወሰደ፤ ህዳር 14 ቀን 2014 ዓ.ም)


Read 1612 times