Saturday, 04 December 2021 13:14

የህክምና ባለሙያው መመሪያ ወይም Guideline ያስፈልገዋል

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

 በአለም አቀፍ ደረጃ ከወሊድ በሁዋላ የሚከሰት የደም መፍሰስ እናቶችን በመግደል ረገድ ከፍተኛውን ደረጃ የያዘ ነው፡፡ እናቶችን በወሊድ ጊዜ ከሚከሰት የደም መፍሰስ አደጋ ለመከላከል የሚደርሰውን ችግር ምክንያቱን በመረዳት ሴቶች ልጅ በሚወልዱበት ወቅት መደረግ ያለበትን ሙያዊ እገዛ ተባብሮ በመስራት ግዴታን መወጣት ከህክምና ባለሙያዎች ይጠበቃል፡፡
በአለማችን እ.ኤ.አ በ2017 የእናቶች ሞት 295,000 ያህል ተመዝግቦአል፡፡
ከተጠቀሰው የሞት መጠን አብዛኛው ማለትም ወደ 86% (254,000) የሚሆነው ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ነው፡፡
በአለም ላይ ከሚከሰተው የእናቶች ሞት (27.1%) ያህሉ የሚያጋጥመው በወሊድ ጊዜ በሚከሰት የደም መፍሰስ ምክንያት ነው፡፡     
በአለም ላይ ከሚከሰተው አጠቃላይ የእናቶች ሞት ውስጥ በHaemorrhage ወይንም በወሊድ ጊዜ በደም መፍሰስ ምክንያት የሚያጋጥመው ከ 24.5%-30.3% ይደርሳል፡፡
በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት የእናቶች ሞት መቀነስ መመዝገቡ እውን ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ1990/ዓ/ም ከነበረበት 69% ዝቅ ቢልም ግን በ2015 እንደታየው አሁንም ከፍ ያለ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ያመላክታል፡፡
እ.ኤ.አ በ2007 በተደረገው የዳሰሳ ጥናት አብዛኞቹ ማለትም ወደ (82%) የሚሆነውን የእናቶች ሞት መከላከል እንደሚቻል ያሳያል፡፡ ሊከላከሉዋቸው ከሚቻሉት የእናቶች ሞት ምክንያቶች ውስጥ በወሊድ ጊዜ የደም መፍሰስ ማለትም Haemorrhage አንዱ ሲሆን በኢትዮጵያ 58% ለሚሆኑ የእናቶች ሞት  ምክን ያት እንደሚሆን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በወሊድ ጊዜ የደም መፍሰስ ማለትም Haemorrhage በኢትዮጵያም በከፍተኛ ሁኔታ ለብዙ እናቶች ሞት ምክንያት ነው፡፡
ህዳር 16 እና 17/2014 በሒልተን ሆቴል አንድ የምክክር ስብሰባ ተካሂዶአል፡፡የስብሰባው አላማም በሀገራችን ከወሊድ በሁዋላ በደም መፍሰስ ምክንያት ሕይወታቸው የሚያልፍን እናቶች ከሞት ለማዳን እንዲቻል ለሕክምና ባለሙያዎች አሰራር እገዛ የሚያደርግ Ethiopia post-partum Haemorrhage Guideline and Care Pathways የተሰኘ መመሪያ ወይንም Guideline በመሰ ራት ላይ ያለ ሲሆን ወደፍጻሜ ለማድረስ እንዲቻል ነው፡፡ ከተለያዩ ሙያ ዎች የተው ጣጡ ባለሙያዎች የተሳተፉበትን የምክክር ስብሰባ በሚመለከት ሀሳባ ቸውን ያካፈሉን ዶ/ር ተስፋዬ ሁሪሳ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የማህጸንና ጽንስ ህክምና ተባባሪ ፕሮፌሰር እና በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በRH &Family Planing Sub Specialist ናቸው፡፡
ዶ/ር ተስፋዬ ሁሪሳ እንደገለጹት ለምክክር ስብሰባው ምክንያት የሆነው ፕሮጀክት በኢትዮ ጵያ በወሊድ ጊዜ እና በተለያዩ ሕመሞች የሚደርስን የእናቶች ሞት የሚመለከት ነው፡፡ የጤናማ እናትነት ባለፈው አመት በ2013 እና በዘንድሮውም ዋናው የትኩረት አቅጣጫው ከወሊድ በሁዋላ በሚከሰት የደም መፍሰስ ምክንያት ሕይወታቸው የሚያልፍን እናቶችን ቁጥር መቀነስ ላይ ታስቦ የዋለና ዘንድሮም በዚህ ዙሪያ ይሆናል ብለን እንጠብቃለን ብለዋል ዶ/ር ተስፋዬ፡፡ የፕሮጀክቱ ዋና አላማ በሴቶች ላይ በተለያየ ምክንያት ማለትም ደህንነቱ ካልተጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ ፤ከኢንፌክሽን እና ከመሳሰሉት ጋር የሚከሰተውን የደም መፍሰስ የቀነስን ሲሆን ከወሊድ ጋር ተያይዞ በሚከሰተው የደም መፍሰስ የሚከሰተውን ሞት ግን እስከአሁን ድረስ መቀነስ አልተቻለም ብለዋል ዶ/ር ተስፋዬ፡፡ ይህ ቁጥር ዛሬም ብዙ ነው፡፡ ይህ ፕሮጀክት ዋና ትኩረቱ እናቶችን በወሊድ ወቅት  እና በተለያዩ ምክንያቶች በሚከሰተው የደም መፍ ሰስ ከመሞት ማዳን ነው፡፡
በወሊድ ጊዜ የሚከሰትን የደም መፍሰስ ለመቀነስ የተለያዩ ዘዴዎች አሉ፡፡ ከእነሱም ወቅ ታዊ መረ ጃዎች ላይ የተመሰረተ ዶክመንት ወይንም መመሪያ አንዱ ነው፡፡ የአለም የጤና ድርጅት ከእናቶች የደም መፍሰስ ጋር ተያይዞ እ.ኤ.አ በ2017--2018 አንድ የስራ መመሪያ አውጥቶአል፡፡ ይህ Guideline ወይንም መመሪያ ግን በአገራችን እስከአሁን ያልተካተተ ሲሆን ይህን ለማድረግ በመንገድ ላይ ነን ብለዋል ዶ/ር ተስፋዬ ሁሪሳ፡፡ በተጨማሪም አሉ ዶ/ር በWHO በእናቶች ጤንነት ዙሪያ በቅርብ የወጣ አዲስ ፕሮቶኮል ያለ ሲሆን ከፕሮ ቶኮሉ ውስጥ ከወሊድ በሁዋላ የእናቶች የደም መፍሰስ የሚለውን ለብቻው ለይቶ የባለሙ ያዎች የስራ መመሪያ Guideline ለማዘጋጀት ከተጀመረ ወደ ስድስት ወር ሆኖ ታል፡፡ ይህን ፕሮጀክት ፤ International federation of Gynaecologists & Obstetrics (FIGO)  International Confederation of Midwives በአገር ውስጥ ደግሞ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር (Ethiopian association of obstetric & Gynaecologists) (ESOG) እና የኢትዮጵያ አዋላጅ ነርሶች ማህበር (Ethiopian Midwives Association) እየመሩት ሲሰራ ቆይቶአል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ሌሎች የሚመለከታቸው አገር በቀል ድርጅቶች ፤የሙያ ማህበራት ፤  የትም ህርት ተቋማት ሁሉ በዚህ ዶክመንት ስራ ላይ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ይህንን ዶክመንት  በመስራት የጎደሉ ሀሳቦችን በማካተት እና በማረም የሰራን ሲሆን በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ ደግሞ የማጠናከሪያ ሀሳቦችን ለመሰብሰብ በዚህ መድረክ ተገናኝተናል ብለዋል ዶ/ር ተስፋዬ ሁሪሳ፡፡ ይህንን ስራ የሚመሩት የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር እና የኢትዮጵያ የአዋላጅ ነርሶች ማህበር ሲሆኑ በዚህ መድረክ ላይ የተጋበዙት ደግሞ ከጤና ጥበቃ ሚኒስ ቴር ፤የህክምና ባለሙያዎች፤ሜሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች፤የሙያ ማህበራት፤ከቅዱስ ጳውሎስ፤ከየካቲት፤ከጥቁር አንበሳ የህክምና መምህሮች፤ከአለም ጤና ድርጅት፤ከአለም የጤና ድርጅት…ወዘተ ናቸው፡፡ ባለሙ ያዎቹ በሁለት ቀን የምክክር ስብሰባ ላይ በመገኘት ዶክመንቱ ምን ጥሩ ጎን አለው የጎደለ ውስ ምንድነው የሚለውን በጥልቀት ተነጋግረዋል፡፡ በአጠቃላይም በእናቶች ጤና ዙሪያ የሚሰሩ ከሀያ በላይ የሚሆኑ ተባባሪ አካላት ተሳትፈውበታል፡፡
ባለሙያ ህክምና ሲሰጥ መመሪያ ወይም Guideline ቢኖረው ጥሩ ነው፡፡ ይህ በመዘጋጀት ላይ ያለው ዶክመንትም የሚያገለግለው የጤና ባለሙያውን ስለሆነ  ባለሙያው በወሊድ ጊዜ ከእናቶች የደም መፍሰስ ጋር በተያያዘ ከጅምሩ አንስቶ በምን አይነት መንገድ ሕክምና መስጠት እንዳለበት፤ምን አይነት መድሀኒት ማዘዝ እንደ ሚገባው የሚያሳይ የእናቶችን ሞት ለማስቀረት የሚያግዝ አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስ ችል አሰራርን ያካተተ ነው፡፡ ስለዚህም ምንጊዜም የጤና ባለሙያ ዎች እንደ መመሪያ የሚጠ ቀሙበት ይሆናል፡፡ ይህ መመሪያ ወይም Guideline ስራው መጠናቀቅ ብቻ የሚቀረው ስለሆነ ቢበዛ ከዚህ በሁዋላ እስከ ሶስት ወር ድረስ ከባለሙያዎች እጅ ይደርሳል የሚል ግምት አለ እንደ ዶ/ር ተስፋዬ ሁሪሳ ማብራሪያ፡፡
Ethiopia post-partum Haemorrhage Guideline and Care Pathways የተሰኘው መመሪያ በብሔራዊ ደረጃ የሚወጣ ሲሆን በመላው አገሪቱ ባሉ የህክምና ተቋማት እንዲ ዳረስ ተደርጎ የሚሰናዳ ነው፡፡ በዚህም መሰረት የእናቶችን በወሊድ ጊዜም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች የሚደርሰውን የደም መፍሰስ በተመለከት ሐኪም፤ነርስ፤አዋላጅ ምን ማድረግ አለበት የሚለውን በተሟላ ሁኔታ በዝርዝር የያዘ ይሆናል፡፡ የእናቶችን በወሊድ ጊዜም ይሁን ተያያዥ በሆኑ ምክንያቶች የሚደርስን የደም መፍሰስ ለመከላከል በተለያዩ ስራ የተሰማሩ ባለሙያዎች ማለትም ክሊኒክ ያላቸው ወይንም በክሊኒክ የሚሰሩ፤በዩኒቨርሲቲ በማስተማር ላይ ያሉ፤ከህክምና ትምህርት ቤት፤ከሙያተኞች ማህበር ከመሳሰሉት የባለሙያዎች ቡድን ሁሉንም የጤና ባለሙያ በሚወክል መልኩ ተቋቁሟል፡፡ ይህ ቡድን መመሪያውን Guideline ስለሰራ የትኛውም ቦታ ላይ ያለውን ወይንም ሁሉንም የጤና ባለሙያ ይወክላል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ስለዚህም ዶክመንቱ ካለቀ በሁዋላ ቀጣዩ ነገር መጠቀም ብቻ ይሆናል፡፡
በስተመጨረሻም ዶ/ር ተስፋዬ ያከሉት ሀሳብ ሁሉም ሴቶች ቅድመ እርግዝና ክትትል እንዲ ያደርጉ ፤ ቅድመ ወሊድ ክትትል እንዲያደርጉ ፤ለመውለድ ወደ ጤና ተቋም እንዲሄዱ እን ደሀገር አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ ስለዚህ እናቶች ከስነተዋልዶ ጤና ጋር በተያያዘ እያንዳን ዱን ገጠመኛቸውን ወደ ጤና ባለሙያ እና ወደ ሕክምና አገልግሎት መስጫ በመቅረብ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ይመከራሉ፡፡ የህክምና ባለሙያዎችም እናቶች እንዳይጎዱ የተ ዘጋጁ መመሪያዎችን መሰረት ያደረገ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጡ አደራ ተጥሎባ ቸዋል ብለ ዋል ዶ/ር ተስፋዬ ሁሪሳ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የማህጸንና ጽንስ ተባ ባሪ ፕሮፌሰር እና በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በRH &Family Planing Sub Specialist.

Read 11276 times