Saturday, 04 December 2021 13:19

የዓለም የህጻናት ቀን በ”ትኩረት ለሴቶች ለህፃናት” አኬዢ መንደር ተከበረ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

   ልዩ ፍላጎት  ያላቸውን ህፃናትና ወላጆቻቸውን ለማገዝ  የተቋቋመው “ትኩረት ለሴቶችና ለህፃናት  ማህበር በኣለም ለ32ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ የተከበረውን የዓለም የህፃናት ቀን በልዩ ልዩ መሰናዶዎች አከበረ። ማህበሩ በኢትዮጵያ ተደራራቢ የጤና ችግር እና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ህፃናትና እናቶቻቸውን በሁለንተናዊ ድጋፍ የተሻለ ህይወት እንዲኖሩ ለማድረግ ከ14 ዓመት በፊት የተቋቋመ ነው። እስካሁን በሺዎች የሚቆጠሩ ልዩ ድጋፍ የሚፈልጉ ህፃናትን ሲያገለግል የቆየውና እያገለገለ ያለው ማህበሩ፣ ባለፈው ሳምንት ከተማ አስተዳደሩ ለማዕከል ግንባታ በሰጠው ከ2 ሺህ በላይ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ (አኬዢያ መንደር) በተለያዩ  መሰናዶዎች ነው የህፃናት ቀኑን ያከበረው። በዕለቱ ከአዲስ አበባ ሴቶችና ህፃናት ቢሮ የመጡ ሃላፊዎች፣ የህፃናት ሀኪሞች፣ የስነ-ልቦና ባለሙያዎችና ማህበሩን በአምባሳደርነት የምታገለግለው አርቲስት አቦነሽ አድነው የተገኙ ሲሆን፣ እምብዛም ትኩረት ባልተሰጠው ልዩ ፍላጎት ያላቸው ህጻትና ወላጆቻቸው ባሉባቸው አርፈ ብዙ ችግሮች ዙሪያ ተወያይተዋል፣ ሀኪሞቹ በዘርፉ ያለውን ተግዳሮትና መፍትሄውን አመልክተዋል።
በመርሃ ግብሩ ማጠናቀቂያም አኬዢያ መንደር በቶሎ ግንባታው ተጠናቅቆ ከኪራይ እንዲወጡ የማህበሩ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲስተር አሳዬች ይርጋ ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።

Read 11452 times