Saturday, 04 December 2021 13:20

“ቀበና በትውስታ ጎዳና” አዲስ መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

   ባለፉት 20 ዓመታት ኑሮውን በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገውና በ20 ዓመታት ውስጥ 26 መፅሐፍን ለንባብ ያበቃው የዲያስፖራው ደራሲ አለማየሁ ማሞ ስራ የሆነው  “ቀበና በትዝታ ጎዳና” መፅሐፍ ለንባብ በቃ።
መፅሐፉ በዋናነት ደራሲው ተወልዶ ያደገበትን ቀበናንና አካባቢውን፣ የልጅነት ትዝታዎቹንና ያሳለፋቸውን ጊዜያት የቃኘበት እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። መፅሐፉ “ ታምሜያለሁና እጅጉን በጠና፣ ሀኪሞች ሰፈር ውሰዱኝ ቀበና” ስለተባለለት ወይም እውቁ አቀንቃኝ ፀሀዬ ዮሐንስ “ቢሻን ቀበና” ብሎ ይቀነቀነለት ቀበናና አካባቢዋ በመጽሐፉ ትልቁን ቦታ እንደያዙም ለማወቅ ተችሏል። በ128 ገጽ የተመጠነው መፅሐፉ በ100 ብርና በ10 ዶላር ለገበያ መቅረቡን ያስታወሰው ደራሲ  አለማየሁ ማሞ ጃዕፈር መፅሐፍት መደብር በዋናነት እንደሚያከፋፍለውም ገልጿል።

Read 11522 times