Tuesday, 07 December 2021 05:30

“ወደ መቀሌ እየተመለሰ ያለው ባቡር”

Written by 
Rate this item
(0 votes)

አገራችንን በአንድ ትልቅ ቤት፣ ሰፊ ግቢ ብንመስላት፣ በቤቱ ትልቅነትና በግቢው ስፋት የሚቀኑት በዙሪያው ያሉት ናቸው። እነሱ አሻግረው ወደ ቤቱ ሊያዩ ይችላሉ። የቤቱ ባለቤቶች የጎረቤታቸውን ትናንሽ ቤቶች እያዩ ያናንቁ እንደሆን እንጂ የራሳቸው ትልቅ ቤትና ሰፊ ግቢ አይታያቸውም። በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ  እኩል ነው አበው እንዲሉ። የቤታቸው ትልቅነት  የሚታያቸው አያምጣው እንጂ ክፉ ጊዜ መጥቶ ቤቱን  ባጡበት ጊዜ ነው የሚሆነው፡፡
የትግራይ ገበሬ የ2013 ዓ.ም ክረምትን በእርሻ  ሥራው እንዲያሳልፍ  በማሰብ መንግስት በራሱ ፈቃድ የአንድ ወገን የተኩስ አቁም እርምጃ ወሰደ። እዚያው ትግራይ ውስጥ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ቦታዎች በቁጥጥሩ ስር አድርጎ የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ ወስዶ ቢሆን ኖሮ፣ አሸባሪው ትሕነግ በየስርቻው የቀበረውን መሳሪያ ለማውጣት፣ በየመንደሩ የበተነውን ወታደር ለማሰባሰብና ለማደራጀት የሚያስችለው ሁኔታ ሊያገኝ ባልቻለም ነበር።
መንግስት ለህዝቡ በማሰብ በቅንነት የወሰደው እርምጃ፣ ለትሕነግ ሠርግና ምላሽ የሆነ ሁኔታ መፍጠሩ ግልጽ ነው። ጦሩን ከኋላ ከኋላ እየተከተለ ጥቃት መፈጸሙ አልበቃ ብሎት ከትግራይ ክልል በመውጣት፣ የአማራና አፋር  አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ጦር ሜዳነት ለወጣቸው።  የጦር ሜዳው ከካሳጊታ እስከ አዶርቃይ ድረስ እንዲዘረጋ አደረገ። በደባርቅ ግንባር ብቻ ከሱዳን ጋር የሚያገናኘውን በር ለማስከፈት ከሃያ ላላነሰ ጊዜ አካባቢውን በመውረር ለመያዝ ቢሞክርም፣ በወገን ጦር እየተመታ እንዲመለስ መደረጉ ይታወቃል።
የአዶርቃይን ግንባር እንደፈለገ የሚሰብረው አለመሆኑን የተገነዘበው ትሕነግ፤ ሌላ አማራጭ አድርጎ የያዘው በአፋር አሳኢታ የሚሌን መስመር መቆጣጠር ነበር። በዚህም ደጋግሞ ሞክሮ  ቀንዱን እየተመታ ተመልሷል። ሶስተኛው የወረራ መስመሩ ወልዲያ፣ ደሴ፣ ከሚሴ መንዝ፣  ሰቆጣ ጋሸና ወገልጤና ቱሉ አውሊያ ፣ ወረኢሉ ወዘተ ሲሆን በዚህ አካባቢ እንደታሰበውና እንደተፈለገው ግስጋሴውን ማስቆም ሳይቻል መቅረቱ ግልጽ ነው።
ደሴና ኮምቦልቻን በእጁ ካስገባ በኋላ አዲስ አበባ በጥቂት ቀናት ውስጥ እጁ ላይ እንደምትወድቅ  በአደባባይ ተናገረ። አሜሪካና እንግሊዝ እንዲሁም የእነሱ አጋሮች፣ መንግሥት፣ ከአሸባሪው ቡድን ጋር ለድርድር በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲቀመጥ ወተወቱ። የልብ ልብ የተሰማው አሸባሪው ትሕነግ፤ “ጦርነቱ አልቋል፤ የምን ድርድር!” ሲል መደንፋቱም ይታወሳል።
ነገር ግን ሕዳር 13 ቀን 2014 ዓ.ም በትሕነግም ሆነ በሌላው ዘንድ ያልተጠበቀ ነገር ሆነ። ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ ወደ ግንባር እንደሚዘምቱና ውጊያውን እንደሚመሩ አስታወቁ፡፡ በነጋታውም በግንባር መሰለፋቸውን ይፋ አደረጉ። የመልሶ ማጥቃት ጦርነቱ በአስራ ሰባት የጦር ሜዳዎች ተከፈተ። የመጀመሪያው ድል በአፋር ግንባር ካሣጊታ በጭፍራ ወዘተ ተመዘገበ። ሸዋ ደብረ ሲና ጫፍ ደርሶ የነበረው ትሕነግ፣ ወደ ኋላ  እንዲመለስ  ተደረገ። በመሐል  ሜዳ  መዘዞ፣ በወረኢሉ ወዘተ እየተቀጠቀጠ ሙትና ቁስለኛ ከመሆን የተረፈው፣ ከገበሬ አሮጌ ልብስ እየሸመተ መሳሪያውን እየሸጠ፣ ነፍሱን ለማትረፍ ማድረግ የሚችለውን ሁሉ  እያደረገ ነው።  ግብፃዊው የፖለቲካ  ተንታኝ እንዳለው፤ “ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ የሚሄደው ባቡር ተጠምዝዞ ወደ መቀሌ እየሄደ ነው”።
የወራሪውና የዘረኛው  ትሕነግ መሸነፍና በወረራ ከያዘው የአማራና የአፋር አካባቢ መውጣት ከሁሉ በፊት ራስ ምታት  የሆነው ለግብጽና አጋሮቿ ነው። ይህ የሆነው ደግሞ በተደጋጋሚ እንደተነገረው፣ ትህነግ እየተዋጋ የነበረው የራሱን ጦርነት ሳይሆን፣ የተገዛበትን የግብፅና የአጋሮቹን ጦርነት  በመሆኑ ነው።ትሕነግ በገባባቸው የአማራና የአፋር አካባቢዎች የፈፀመው ግፍ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። በአፋር ክልል ከአራት መቶ አርባ በላይ፣ በአማራ ክልል ከአንድ ሺህ ስድስት መቶ በላይ ትምህርት ቤቶች በሙሉና በከፊል እንዲወድሙ አድርጓል። የፈረሱት የጤና ኬላዎች፣ የጤና ጣቢያዎችና መካከለኛ ሆስፒታሎች ገና ተቆጥረው የሚደረስባቸው ናቸው። ሌሎች ሕዝባዊና መንግስታዊ ተቋማትም  ላይ ቢሆን የተፈጸመው ተመሳሳይ ነው።ግብጾች እየጨነቃቸው እንደተናገሩትና በተግባር እየታየ እንዳለው፣ ባቡሩ ሰሜን ሸዋ ደርሶ የመልስ ጉዞውን ወደ መቀሌ እያደረገ ነው። መቀሌ መግባት ያለበት ግን የጫነውን ሁሉ በአማራና በአፋር ክልል አራግፎ ባዶውን ነው። ባዶውን መግባት ብቻ ሳይሆን መቀሌ ለአሸባሪው የትሕነግ ሃይሎች መቀበሪያቸው  እንዲሆናቸው ተደርጎ ነው።
“ዘመቻ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት” ከመጀመሩ በፊት የአማራ ክልል ባደረገው ጥናት፣ በአሸባሪው ትሕነግ ወረራ ተይዘው በተለቀቁ አካባቢዎች፣ ሁለት መቶ ሰማኒያ ቢሊዮን ብር የሚገመት የንብረት ጉዳት ማድረሱ ይፋ መደረጉ  ይታወሳል። ከወልዲያ እስከ አጣዬ፣ ከሰቆጣ እስከ ከላላ መሀል ሜዳ  ወዘተ ድረስ ባለው አካባቢ ያደረሰው ጉዳት  ወደፊት ተጣርቶ እንደሚገለጽ ይጠበቃል። የጦር ጉዳት ካሳውን ማነው የሚከፍለው?
ካሣ ሊከፈልበት የሚገባው ግን ደግሞ በምን መንገድ ማካካስ እንደሚቻል ለማሰብና ለመናገር የሚከብደው  በተያዙ አካባቢዎች በሚኖሩ ሰዎች አእምሮ፣ አካልና ሕይወት ላይ የደረሰው ጉዳት ነው። ነገሩ በጭራሽ ዝም ተብሎ የሚታለፍ አይደለም።ትሕነግና የትግራይ ሕዝብ አይነጣጠልም፣ አንድ ናቸው ብለው ሲከራከሩ  የነበሩት ተጋሩ፤ የአሸባሪውን የትሕነግ ወንጀል የመሸከም የውዴታ ግዴታ እንዳለባቸው በግልጽ አማርኛ ሊነገራቸው ይገባል፡፡ ትሕነግ በሚጠየቅበት የደም ዋጋ እነሱም ይጠየቃሉ። አማራውና አፋሩ የደም ዋጋው በእነሱ እጅ ላይ ነው።ሰሞኑን አንድ የደሴ ሰው፤ “ብዙ ጊዜ የአንድ ጦር ደጀን የሚገኘው ከኋላ ነው። በሽብርተኛው ትሕነግ ጊዜ ግን እንደዚህ አይደለም። የትሕነግ ደጀን ጦር ያለው ትግራይ ውስጥ ሳይሆን ከትግራይ ውጪ ባለው አካባቢ ሁሉ  ነው” ሲሉ የገለጹትን ሀሳብ ማስታወስ ያስፈልጋል። ትሕነግን በጦርነት ከአማራና ከአፋር ክልል አስወጥቶ በትግራይ መሬት እንዲቀበር ማድረግ ብቻ  የነገሩ መጨረሻ አይሆንም። መሐል አገር በየቦታው አድፍጦ ለትሕነግ እያገለገለ ያለ ሁሉ ተገቢ ቅጣቱን እንዲያገኝ ማድረግ ያስፈልጋል። በዚህ ጊዜ በእርግጥም ባቡሩ ወደ ትግራይ ይመለሳል፤ በትግራይ መሬትም አፈር ይለብሳል።Read 1232 times