Tuesday, 07 December 2021 05:36

ተመድ ዘንድሮ ለ183 ሚ. ሰዎች የነፍስ አድን ድጋፍ 41 ቢ. ዶላር ያስፈልገኛል አለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፈረንጆች አመት 2022 በተለያዩ የአለማችን አገራት ለሚገኙ የነፍስ አድን ድጋፍ የሚሹ 183 ሚሊዮን ያህል ሰዎች የሚውል 41 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው የገለጸ ሲሆን፣ ድርጅቱ በታሪኩ ያቀረበው ከፍተኛው የድጋፍ ጥሪ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ድርጅቱ ባለፈው ረቡዕ ባወጣው መግለጫ እንዳለው፣ በመጪው የፈረንጆች አመት 2022 በመላው አለም በሚገኙ የእርስ በእርስ ግጭት፣ የርሃብ፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ቀውሶች የተከሰቱባቸው አገራት የሚኖሩ 183 ሚሊዮን ያህል ሰዎች አስቸኳይ የነፍስ አድን ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ለጋሾችና አለማቀፉ ማህበረሰብ ለእነዚህ ዜጎች የሚያስፈልገውን 41 ቢሊዮን ዶላር ለማሟላት በአፋጣኝ ርብርብ ማድረግ ካልቻሉ፣ አለማችን ወደ ከፋ ቀውስ ልትገባ እንድምትችል ድርጅቱ አስጠንቅቋል፡፡በአመቱ ከፍተኛ ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው የአለማችን አገራት መካከል የአንደኛ ደረጃን የያዘችው ለ24 ሚሊዮን ያህል ዜጎቿ 4.5 ቢሊዮን ዶላር የምትሻው አፍጋኒስታን ስትሆን ሶርያ፣ የመን፣ ኢትዮጵያና ሱዳን እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ መያዛቸውንም ድርጅቱ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡


Read 7591 times