Saturday, 11 December 2021 13:01

“ፎከስ ኦን አቢሊቲ” አለማቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ዛሬ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

መቀመጫውን ሲድኒ አውስትራሊያ ያደረገውና ትኩረቱን በአካል ጉዳተኞች ላይ ያደረገው “ፎከስ ኦን አቢሊቲ” ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ዛሬ ይከፈታል፡፡ ባለፉት 13 ዓመታት ትኩረቱን በአካል ጉዳተኞች ላይ አድርጎ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በ “አይዲያል ኤቫንትስ” አማካኝነት በኢትዮጵያ ዛሬና ነገ በቫምዳስ ሲኒማና በሀያት ሬጂንስ ሆቴል እንደካሄድ አዘጋጆች ባለፈው ሰኞ ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም ረፋድ ላይ በአዜማን ሆቴል በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
በፌስቲቫሉ ትኩረታቸውን በአካል ጉዳተኝነት ያደረጉትና በአካል ጉዳተኛ ጥበበኞች የተሰሩ ሃገር በቀል 33 አጫጭር ፊልሞችና የውጭ ሀገር ፊልሞችን አሰባስቦ የሚያቀርብ ሲሆን በፌስቲቫሉ ላይ በአካል ጉዳተኞች ጥበበኞች የተሰሩ ስራዎች የሚቀርቡበት አውደ ርዕይ፣ ወጣት ፊልም ሰሪዎች ከአንጋፋዎቹ ጋር የሚገኛኙበት የውይይትና ጥያቄና መልስ መድረክና ሀገር በቀል ፊልሞችን ለማበረታታትና ለማስተዋወቅ ፊልሞችን አወዳድሮ አሸናፊዎችን በደማቅ ስነ-ሥርዓት የመሸለም መርሃ ግብሮች እንደሚካሄዱ የ“አይዲያል ኤቨንትስ” ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሚኪያስ ሙሉጌታ ተናግረዋል፡፡

Read 11504 times