Saturday, 11 December 2021 13:01

የታገል ሰይፉ “የልቤ ክረምቱ” የግጥም መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(3 votes)

    የገጣሚ ታገል ሰይፉ “የልቤ ክረምቱ ቅፅ 1” የተሰኘ አዲስ የግጥም ስብስብ መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡ መፅሐፉ የገጣሚውን የመጀመሪያ “ፍቅር” የተሰኘውን የግጥም መፅሐፍ የተፃፈበትን 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ “ፍቅር”፣ “ቀፎውን አትንኩት”፣ “በሚመጣው ሰንበት” ከተሠኙ  ቀደምት መፅሐፎቹ የተወጣጡና በመፅሐፉ ያልታተሙ ስሶስት ግጥሞችን ጨምሮ ከሁለት ዓመታት በፊት ቢያሰናዳም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ለገበያ አለመቅረቡንም ገጣሚ ታገል ሰይፉ ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡
“ፍቅር” የተሰኘው የመጀመሪያው የግጥም መፅሐፉ በ1982 ዓ.ም ገና በ14 ዓመቱ ለንባብ መብቃቱ የሚታወስ ሲሆን በአሁኑ መፅሐፍ 32 ዓመት ሆኖታል፡፡
ገጣሚው “የልቤ ክረምቱ” በተኘውና ከቀደሙት አራቱ የግጥም መፅሀፍቱ የተውጣጡና ያልታተሙ ሶስት አዳዲስ ግጥሞችን ጨምሮ 61 ግጥሞች በመፅሐፉ የተካተቱ ሲሆን “ግጥም” በታገል ሰይፉ እይታ ምን ይመስላል የሚለውን ለአንባቢያን ለመግለፅ ትንታኔ መጨመሩንም ታገል ሰይፉ ገልጿል በ122 ገፅ የተቀነበበው መፅሐፍ በ100 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በመፅሀፉ አይረሴ ባለውለታዎቹንም አስታውሶ አመስግኗል፡፡

Read 21680 times