Saturday, 11 December 2021 14:00

የአለማችን ቢሊየነሮች 1.6 ትሪሊዮን ዶላር ሃብት አፍርተዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

  በመላው አለም የሚገኙ ከ2 ሺህ 600 በላይ እጅግ ባለጸጋ ቢሊየነሮች በፈረንጆች አመት 2021 ብቻ ተጨማሪ 1.6 ትሪሊዮን ዶላር ሃብት ማፍራታቸውንና አጠቃላይ የሃብት መጠናቸው 13.6 ትሪሊዮን ዶላር መድረሱን ፎርብስ መጽሄት አስነብቧል፡፡
በአመቱ እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለው የሃብት ጭማሬ ያስመዘገቡት የአለማችን ቁጥር አንድ ቢሊየነር ኤለን መስክ ሲሆኑ፣ ሃብታቸው በ156 ቢሊዮን ዶላር በመጨመር 266 ቢሊዮን ዶላር መድረሱንም ዘገባው አመልክቷል፡፡
ከአገራት አንጻር ከፍተኛ የሃብት ጭማሬ ያስመዘገቡት የአሜሪካ ቢሊየነሮች መሆናቸውን የጠቆመው ፎርብስ፣ ባለጸጎቹ ባለፉት 12 ወራት በድምሩ 495 ቢሊዮን ዶላር ማፍራታቸውን የገለጸ ሲሆን፣ ህንዳውያን ቢሊየነሮች በ210 ቢሊዮን ዶላር፣ ሩስያውያን ቢሊየነሮች ደግሞ በ145 ቢሊዮን ዶላር ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ መያዛቸውንም አመልክቷል፡፡


Read 1807 times