Sunday, 12 December 2021 00:00

የናፖሊዮን ሰይፍና 5 ሽጉጦች በ2.8 ሚ. ዶላር ተሸጡ

Written by 
Rate this item
(0 votes)


            ፈረንሳዊው ንጉስ ናፖሊዮን ቦናፓርት እ.ኤ.አ በ1799 የተካሄደውን አብዮት በመራበት ወቅት የተጠቀመባቸው አንድ ሰይፍና አምስት ሽጉጦች ሰሞኑን አሜሪካ ውስጥ ለጨረታ ቀርበው በ2.8 ሚሊዮን ዶላር መሸጣቸው ተነግሯል፡፡
ተቀማጭነቱ በኢሊኖይስ በሆነው ሮክ አይስላንድ የተባለ አጫራች ኩባንያ አማካይነት ለጨረታ የቀረቡትን እነዚህ ቁሳቁሶች አሸንፎ በእጁ ያስገባው ግለሰብ ማንነት ለጊዜው አለመታወቁን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡
ናፖሊዮን ንግስናውን ከጨበጠ በኋላ ታሪካዊ እንደሆነ የተነገረለትን ሰይፍ አንድ የአገሪቱ ጄኔራል በስጦታ መልክ ማበርከቱን ያስታወሰው ዘገባው፣ የጄኔራሉ ሚስት ግን ከአመታት በኋላ ዕዳዋን ለመክፈል ባለመቻሏ ሰይፉን ላልታወቀ ሰው ለመሸጥ መገደዷንና ከረጅም ጊዜ በኋላም በለንደን ወደሚገኝ አንድ ሙዚየም መግባቱን አክሎ ገልጧል፡፡

Read 2663 times