Print this page
Monday, 13 December 2021 00:00

የሮሂንጋ ስደተኞች ፌስቡክን በ150 ቢሊዮን ዶላር ከሰሱ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በማይንማር በተከሰተው የእርስ በእርስ ግጭት የተፈናቀሉ የሮሂንጋ ስደተኞች፣ የጥላቻ ንግግሮች በስፋት ሲሰራጩና ለግጭቱ መባባስ ምክንያት ሲሆኑ ተገቢውን እርምጃ አልወሰደም በማለት በፌስቡክ ላይ የ150 ቢሊዮን ዶላር ካሳ የሚጠይቅ ክስ መመስረታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እ.ኤ.አ በ2017 በማይንማር የተቀሰቀሰው አስከፊ ግጭት ከ10 ሺህ በላይ የሮሂንጋ ሙስሊሞች እንዲገደሉ፣ እንዲደፈሩ፣ ቤት ንብረታቸው እንዲቃጠልና ከ730 ሺህ በላይ የሚሆኑትም አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ምክንያት መሆኑን ያስታወሰው ዘገባው፤ ፌስቡክ እንደ ማህበረሰብ የጥፋት አዋጅ ሲታወጅብን ዝም ብሎ በማየት ለከፋ ጥፋት ዳርጎናል ያሉ ስደተኞች ባለፈው ሰኞ ካሊፎርኒያ በሚገኝ ፍርድ ቤት ክሳቸውን ማቅረባቸውን አመልክቷል፡፡

Read 2644 times
Administrator

Latest from Administrator