Print this page
Wednesday, 15 December 2021 00:00

ኮሮና 100 ሚ. የአለማችን ህጻናትን ለድህነት ዳርጓል ተባለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

     ከ1.6 ቢሊዮን በላይ ህጻናት በወረርሽኙ ሳቢያ ትምህርት አቋርጠዋል

             የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ባለፉት 75 አመታት ታሪኩ የአለማችንን ህጻናት በከፋ ሁኔታ ተጎጂ በማድረግ ረገድ የኮሮና ቀውስን የሚስተካከል እንደሌለና፣ ወረርሽኙ 100 ሚሊዮን የአለማችን ህጻናትን ወደ ድህነት ማስገባቱን አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ የተመሰረተበትን 75ኛ አመት ምክንያት በማድረግ ሰሞኑን ይፋ ባደረገው አለማቀፍ ሪፖርት እንዳለው፣ በመላው አለም ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው ከ1.6 ቢሊዮን በላይ ህጻናት ከትምህርት ገበታቸው ውጭ ለመሆን ተገድደዋል፡፡
ወረርሽኙ የፈጠረው ጫና ህጻናት በቂ ህክምና እንዳያገኙ ብሎም የአእምሮ ህመምን ጨምሮ ለተለያዩ የጤና ችግሮች ተጋላጭ ማድረጉን የጠቆመው ሪፖርቱ፣ እ.ኤ.አ በ2020 በመላው አለም የሚገኙ ከ23 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ኮሮና በፈጠረው ጫና ምክንያት መደበኛ ክትባቶችን ሳያገኙ መቅረታቸውንም አክሎ ገልጧል፡፡
የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ ሰለቦች የሆኑ የአለማችን ህጻናት ባለፈው አመት ከነበረበት በ8.4 ሚሊዮን በመጨመር ዘንድሮ 160 ሚሊዮን ደርሷል ያለው ድርጅቱ፤ ከኮቪድ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ እስከ መጪዎቹ ስምንት አመታት ጊዜ ድረስ ተጨማሪ 10 ሚሊዮን ያህል ህጻናት ያለዕድሜያቸው ሊዳሩ እንደሚችሉም ግምቱን አስቀምጧል።

Read 6348 times
Administrator

Latest from Administrator