Monday, 20 December 2021 00:00

ባራክ እና ሚሼል የአመቱ የአለማችን ድንቅ ሰዎች ተብለዋ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

  በየአመቱ በመላው አለም አድናቆትና ዝናን ያተረፉ የአለማችን ታዋቂ  ሰዎችን ዝርዝር ይፋ የሚያደርገው ዩጎቭ የተባለው አለማቀፍ የጥናት ተቋም፣ ከሰሞኑም የዘንድሮውን ሪፖርት ይፋ ያደረገ ሲሆን የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እና ባለቤታቸው ሚሼል ኦባማ ዘንድሮም የአመቱ የአለማችን ድንቅ ሰዎች ተብለዋል፡፡
ባራክ ኦባማ የአለማችን ድንቅ ወንድ ተብለው ሲመረጡ የአምናውን ጨምሮ ይህ ሁለተኛ ጊዜያቸው መሆኑን ያስታወሰው ተቋሙ፣ ሚሼል ኦባማ በበኩላቸው የዘንድሮውን ጨምሮ ለ3 ተከታታይ አመታት የአለማችን እጅግ ተደናቂ ሴት መሆናቸውን ገልጧል፡፡
ተቋሙ በ38 የአለማችን አገራት የሰራውን ጥናት መሰረት አድርጎ ባወጣው የ2021 የፈረንጆች አመት የአለማችን ድንቅ ሰዎች ዝርዝር በወንዶች ዘርፍ ሁለተኛ ደረጃን የያዙት አሜሪካዊው ቢሊየነር ቢል ጌትስ ሲሆኑ፣ የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ዢ ጂፒንግ ሶስተኛ ደረጃን መያዛቸው ተነግሯል፡፡ ከአራተኛ እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ የያዙት ደግሞ ፖርቹጋላዊው የአለማችን የእግር ኳስ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ቻይናዊው የፊልም ተዋናይ ጃኪ ቻን፣ አሜሪካዊው ቢሊየነር ኤለን መስክ፣ አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ፣ የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እና የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ናቸው፡፡
ከሚሼል ኦባማ በመቀጠል የአመቱ 2ኛ ተደናቂዋ ሴት የተባለችው ታዋቂዋ የፊልም ተዋናይት አንጀሊና ጆሊ ስትሆን፣ የእንግሊዟ ንግስት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ በበኩላቸው የሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡ በሴቶች ዘርፍ ከአራተኛ እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ የያዙት ደግሞ፣ ኦፕራ ዊንፍሬይ፣ ስካርሌት ጆንሰን፣ ኢማ ዋትሰን፣ ቴለር ስዊፍት፣ አንጌላ መርኬል፣ ማላላ ዩሱፋዚና ፕሪያንካ ቾፕራ መሆናቸው ተነግሯል፡፡


Read 1147 times