Print this page
Monday, 20 December 2021 00:00

አፕል የመጀመሪያው ባለ 3 ትሪሊዮን ዶላር ኩባንያ ሊሆን ተቃርቧል

Written by 
Rate this item
(0 votes)


             የአይፎን ስልክ አምራቹ የአሜሪካ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል በአለማችን የንግድ ኩባንያዎች ታሪክ አጠቃላይ የገበያ ዋጋው ወይም ሃብቱ 3 ትሪሊዮን ዶላር የደረሰ የመጀመሪያው ኩባንያ ለመሆን መቃረቡን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
በነሐሴ ወር 2018 በአለማችን የኩባንያዎች ሃብት ታሪክ አጠቃላይ የገበያ ዋጋው ከ1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው የአለማችን ኩባንያ ሆኖ የተመዘገበው አፕል፣ ከሁለት አመታት በኋላም ሃብቱ ከ2 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው ኩባንያ ሆኖ መመዝገቡን ያስታወሰው ዘገባው፣ ኩባንያው አሁን ደግሞ ከ3 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ሃብት በማፍራት ሃትሪክ ሊሰራ መቃረቡን አመልክቷል፡፡ የአፕል የአክሲዮን ገበያ ዋጋ ባለፈው ሳምንት በ11 በመቶ ያህል ማደጉን ያስታወሰው ዘገባው፣ አርብ እለት የኩባንያው አጠቃላይ የገበያ ዋጋ 2.944 ትሪሊዮን ዶላር መድረሱንና የመጀመሪያው ባለ 3 ትሪሊዮን ዶላር ኩባንያ ሆኖ በታሪክ መዝገብ ለመስፈር ጥቂት እንደቀረው አስነብቧል፡፡
በአሁኑ ከአፕል በመቀጠል ከፍተኛ የገበያ ዋጋ ያለው የአለማችን እጅግ ሃብታም ኩባንያ 2.6 ትሪሊዮን ሃብት ያፈራው ማይክሮሶፍት ሲሆን፣ የጎግል ባለቤት የሆነው አልፋቤት በ2 ትሪሊዮን ዶላር፣ አማዞን በ1.7 ትሪሊዮን ዶላር፣ ቴስላ በ1 ትሪሊዮን ዶላር ሃብት እንደሚከተሉም መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Read 2722 times
Administrator

Latest from Administrator