Print this page
Saturday, 18 December 2021 15:12

የደረጀ በላይነህ የልጆች አነቃቂ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

   በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ለረዥም ዓመታት የተለያዩ መጣጥፎችን በተለይም ሥነጽሁፋዊ ሂሶችን በማቅረብ የሚታወቀው ገጣሚና ደራሲ ደረጀ በላይነህ፤ #ታላላቆቹ; የተሰኘ የልጆች አነቃቂ መጽሐፍ ለገበያ አቅርቧል፡፡ መጽሐፉ አሥር የአገራችንና የዓለም ታላላቅ ሰዎችን ታሪክ የያዘ ሲሆን ባለታሪኮቹ በሳይንስ÷በኪነ ጥበብ÷ በበጎ አድራጎትና በነፃነት ታጋይነት ስኬትና ዕውቅናን የተቀዳጁ ናቸው ተብሏል፡፡
ከውጭዎቹ ሊዎናርዶ ዳ ቪንቺ ÷ቤትሆቨን÷ቶማስ አልቫ ኤዲሰን÷ሐሪየት ትሩማንና አብርሃም ሊንከን የተካተቱ ሲሆን ከሃገራችን ደግሞ አብዲሳ አጋ÷ዶክተር ለገሠ ኦትሮ÷ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት ተክለማርያም÷አርቲስት ዓለምፀሐይ ወዳጆና ዶክተር  ካትሪን  ሐምሊን ተካትተውበታል::
መጽሐፉ ለልጆች የተዘጋጀ እንደመሆኑ የጀርባ አስተያየቱን (Blurb) የጻፉት ሁለት የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች መሆናቸውን ደረጀ በላይነህ ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ ልጆች የታላላቅ ስኬታማ ሰዎችን ታሪክ በለጋ ዕድሜያቸው እያነበቡ፣ አርአያነታቸውንና ፈለጋቸውን እንዲከተሉ ማነቃቃት ነው ብሏል - አዘጋጁ፡፡
በ60 ገፆች ተቀንብቦ ለልጆች በሚማርክ ቀላል ግን ውብ ቋንቋ የተዘጋጀው #ታላላቆቹ; የተሰኘው መጽሐፍ፤  በጃፋር መጻሕፍትና አራት ኪሎ በሚገኘው ቡክ ላይት የመጻሕፍት መደብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡  
ደራሲ ገጣሚና ሃያሲ ደረጀ በላይነህ፣ ከዚህ ቀደም አሥር መጻህፍትን ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡



Read 11331 times
Administrator

Latest from Administrator